በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተግባራት ተመዝግቧል- ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተግባራት መከናወናቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝቦች ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዕቅድ ዝግጅት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ክልሉ ከተመሠረተበት ማግስት ጀምሮ ሲንከባለሉ የመጡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በተገቢው መልኩ መመለስ መቻሉን በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
በክልሉ የተረጋጋና አካታች የፖለቲካ ምህዳር በመፈጠሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በከፍተኛ ሁኔታ ሃሳባቸውን ለህዝብ አድረሰው መወዳደር እንዲችሉ ማድረግ በመቻሉ ሀገራዊ ምርጫው ኢትዮጵያን አሸናፊ ያደረገ እንዲሆን አስችሏል ብለዋል።
እስከታችኛው መዋቅር ድረስ የወረደና የተደራጀ ድጋፍና ክትትል በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥና ቀልጣፋ መንግስታዊ አገልግሎት ማድረስ ስለ መቻሉም ዶ/ር ኢንጂነር ጋሽ ገልፀዋል።
አመራሩ በመንግሥትና ፓርቲ ተግባራት ላይ ወጥ ግንዛቤ እንዲኖረው መደረጉንም የገለጹት ዶ/ር ነጋሽ፣ በየደረጃው የሚገኙ የአመራርና አባላትን እንዲሁም የተቋማትን የማስፈጸም አቅም ማሳደግ መቻሉንም ጠቁመዋል።
በመሰረተ ልማት በኩል በተሰጠው ልዩ ትኩረት የክልሉን ህዝብ ባማከለ መልኩ መገንባት በመቻሉ ከክልሉ ስኬቶች መካከል ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ በተለይም በመንገድ፣ በድልድይ፣ በጤና ፣ በትምህርት፣ በመስኖና በሌሎች በርካታ ፕሮጀክቶችን መከናወናቸውን ጠቁመው፥ ይኽው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።
የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ከፍተኛ ምርት መሰብሰብ ትኩረት የተሰጠበት ነበር ያሉት ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ፥ በዚህም በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በሻይ ልማትም ጥሩ ዉጤት ተመዝግቧል ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ፣ በበጀት ዓመቱ 61 ሺህ የታጠበና ያልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገቢያ መቅረቡንም ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪም 348 ኪ.ግ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ የተቻለ ሲሆን የክልሉን የዉስጥ ገቢ ለማሳደግ በተደረገዉ ሰፊ ርብርብም ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ትልቅ እምርታ ነዉ ብለዋል።
በሌላ በኩል የገቢ መሰረትን በማስፋትና አሟጦ በመሰብሰብ የክልሉን የገቢ አቅም ማሰደግ የተቻለ በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በክልሉ በሁሉም ዘርፎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህም ሂደት የኅብረተሰብ ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከቦንጋ ማስተባበሪያ

More Stories
የገጠር ኮሪደር ልማት ስራዎች የአርሶአደሩን አኗኗር ከማሻሻል ባለፈ የዜጎችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጠ የላቀ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ
ለአገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ዕድገት አሁን እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ምክክር እጅግ ወሳኝና ታሪካዊ ዕድል መሆኑን የሆሳዕና ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ተናገሩ
በ2018/19 መኸር እርሻ ከ30 ሺህ 9 መቶ በላይ ሄክታር መሬት በተለያዩ አዝርዕት ለመሸፈን መታቀዱን የሀላባ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ