ከ230 ሺህ በላይ ዜጎች የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ መውሰዳቸውን የሀላባ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ አስታወቀ
የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ በመያዛቸው በተለያዩ የአገልግሎት ማዕከላት ተገቢውን አገልግሎት ያለእንግልት ለማግኘት እንዳስቻላቸው ያነጋገርናቸው የዞኑ ነዋሪዎች ገልፀዋል::
የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ከዜጎች የማንነት መገለጫነት ባሻገር ከተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ጋር ትስስሩ የጎላ በመሆኑ ፋይዳው ዘርፈ ብዙ ነው ብለዋል::
በሀላባ ዞን የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አበበ አሊዬ እንደገለፁት የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ዘርፈ ብዙ ሀገራዊ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመው፥ በዞኑ በሁሉም አከባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ ሰፊ ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል::
በዚህም በዞኑ እስከአሁን ድረስ ባለው ከ230ሺህ በላይ ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ በመውሰዳቸው የዕቅዱን 60 በመቶ መሸፈን እንደተቻለም ኃለፊው ጠቁመዋል::
የፈይዳ መታወቂያ በተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመሠረታዊነት አስፈላጊ መሆኑን ተከትሎ የዜጎችን የንግድና መሰል ፋይናንሻል እንቅስቃሴዎችን ወደ ዲጅታል ሥርዓት በማስተሳሰር እንደ ሀገር የተቀመጠውን ተልዕኮ ለማሳካት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል ኃላፊው::
የፋይዳ መታወቂያ የዲጅታል መረጃ ደህንነትና የንግድ እንቅስቃሴን እንዲሁም ሌሎች ዘርፈ ብዙ ሀገራዊ መረጃ አያያዝ ሥርዓቶችን ለማዘመን የሚረዳ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንደሆነም አቶ አበበ ገልፀዋል::
የፋይዳ ድጅታል መታወቂያ የምዝገባ ሥርዓቱ እስከ ታችኛው የቀበሌ መዋቅወር ተደራሽ በመሆኑ ያልወሰደው የገጠር ማህበረሰብና አርሶአደሩ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ልወስድ ይገባል ብለዋል::
አቶ አበበ አክለውም ሀገሪቱ በሚታደርገው የዲጅታል ሽግግር ዜጎች የሚጠበቅባቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባም ጥሪ አድርገዋል::
ያነጋገርናቸው ግለሰቦች በበኩላቸው የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ በወቅቱ በመያዛቸው በተለያዩ የአገልግሎት ተቋማት ተገቢውን አገልግሎት ያለ እንግልት እያገኙ ስለመሆናቸው ተናግረዋል::
ዘጋቢ: አብዱልሰመድ አወል – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው