በ2018 ከደረጃ “ለ” ከ13 ሺህ 300 ግብር ከፋዮች ከ80 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዷል – በሀላባ ዞን የቁሊቶ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 02/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በ2018 ከደረጃ “ለ” ከ13 ሺህ 300 ግብር ከፋዮች ከ80 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ተግባር መግባቱን በሀላባ ዞን የቁሊቶ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት አስታወቀ::
የ2018 ማጠናቀቂያ የግብር መክፈያ መርሃ-ግብር በቁሊቶ ከተማ በ5 ማዕከላት በይፋ ተጀምሯል::
የከተማው ምክትል ከንቲባ እና ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሎላሶ እንዳሉት፤ ገቢ የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ መሠረት መሆኑን አመላክተው፥ በዚህም ለከተሞች ዕድገትና ሁለንተናዊ ልማት ጉልህ አበርክቶ አለው ብለዋል::
ግብር ከፋዮቹ ከትላንት ጀምሮ በሁሉም ማዕከላት ግብርን በአግባቡ እየከፈሉ መሆናቸውን ኃላፊው ጠቁመው፥ በዘንድሮው ዓመት ከደረጃ “ለ” 13ሺህ 300 ግብር ከፋዮች ከ80 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱንም አቶ አብዱልቃድር አስታውቀዋል::
ግብርን በወቅቱና በታማኝነት መክፈል ሀገራዊ ግዴታ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ግብር ከፋይ ግዴታውን በመወጣት በከተማዋ ብሎም በሀገር ልማትና ዕድገት ላይ የድርሻውን አሻራ ሊያሳርፍ ይገባልም ብለዋል::
የከተማው ግብር ከፋዮችም ግብር ሀገራዊ ግዴታ መሆኑን በመገንዘብ በወቅቱና በታማኝነት እየከፈሉ ስለመሆናቸው ገልፀዋል::
ዘጋቢ፡ አብዱልሰመድ አወል – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የአርባምንጭ ከተማ ሰላማዊና በተፈጥሮ ፀጋ የበለፀገለች መሆኗ ለቱሪዝም ዘርፍ ተመራጭ ያደርጋታል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ
የሀለባ ዞን ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ቢልዮን 293 ሚልዮን ብር ባለይ በጀት አጸደቀ
መስራት እየቻሉ የገንዘብ እጥረት የገጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ችግሮች ለመፍታት የህብረት ስራ ማህበራት ሚና ቀላል አለመሆኑ ተገለጸ