የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የመንግሥትን ወጪና የልማት ፍላጎት ለመሸፈን በ2019 በጀት ዓመት 14 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም(ደሬቴድ) በአሪ ዞን የጂንካ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽህፈት ቤት እና የንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት የ2018 ዓ.ም የደረጃ “ሀ” እና” ለ” ግብር ማስከፈያ እንዲሁም የ2019 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ እድሳት መርሃ ግብርን በጂንካ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነፃነት አካለወልድ፤ በክልሉ የውስጥ ገቢ አቅም ማደጉን ገልፀው የመንግስት ወጪ እና የሕዝቡን የልማት ፍላጎት ለመሸፈን የሚያግዝ 14 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ሀብት እንደ ክልል ይሰበሰባል ብለዋል።
የአሪ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ታደለች ምክሬ በማስጀመሪያ መድረኩ እንደተናገሩት፤ በዞኑ በሁሉም መዋቅሮች ከሚገኙ ከ42 ሺህ በላይ የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን አስረድተዋል።
የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደግፌ ጌታቸው፤ እያደገ የመጣውን የሕዝቡን የተለያዩ የልማት ፍላጎትን ለማሟላት የከተማ አስተደዳደሩ ገቢን አሟጦ መሰብሰብ ላይ ትኩረት ማድረጉን አስረድተዋል።
በገቢ አሰባሰብ ወቅት የሚታዩ ችግሮችን ለመከላከልና ከመቶ ፐርሰንት በላይ ገቢ ለመሰብሰብ አስፈላጊው ቅድመዝግጅት መደረጉን የገለጹት ደግሞ የጂንካ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማንጎ ከበደ ናቸው።
በ2018 የግብር ዘመን ግደታቸውን በታማኝነት ለተወጡ ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች የማበረታቻ ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የአርባምንጭ ከተማ ሰላማዊና በተፈጥሮ ፀጋ የበለፀገለች መሆኗ ለቱሪዝም ዘርፍ ተመራጭ ያደርጋታል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ
የሀለባ ዞን ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ3 ቢልዮን 293 ሚልዮን ብር ባለይ በጀት አጸደቀ
መስራት እየቻሉ የገንዘብ እጥረት የገጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ችግሮች ለመፍታት የህብረት ስራ ማህበራት ሚና ቀላል አለመሆኑ ተገለጸ