አርሰናል ግብ ጠባቂ ሊያስፈርም ነው
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አዲስ ግብ ጠባቂ ወደ ስብስቡ ለመቀላቀል ተዘጋጅቷል።
መድፈኞቹ ወደ ስብሰባቸው ለመቀላቀል የተዘጋጁት ፈረንሳዊውን ግብ ጠባቂ ኢላን ሜስሊየርን ነው።
ኢላን ሜስሊየር በሊድስ ዩናይትድ የነበረው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ከክለቡ የወጣ ሲሆን ሌላኛውን የእንግሊዝ ክለብ አርሰናል በነፃ ዝውውር ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ ደርሷል።
ግብ ጠባቂ በኢላንድ ሮድ በነበረው የሰባት ዓመታት ቆይታው 215 ጨዋታዎችን ተሰልፎ አከናውኗል።
የ26 ዓመቱ ሜስሊዬር በቀጣይ የህክምና ምርመራውን አጠናቆ አርሰናልን የሚቀላቀል ከሆነ ከሁለቱ ስፔናዊያን ግብ ጠባቂዎች ዳቪድ ራያ እና ኬፓ አሪዛባላጋ ጋር ለቋሚ ተሰላፊነት ይፎክራል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።