በጌዴኦ ዞን ጨለለቅቱ ከተማ አስተዳደር የ2015 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጀመረ

በጌዴኦ ዞን ጨለለቅቱ ከተማ አስተዳደር የ2015 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጀመረ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ)በጌዴኦ ዞን ጨለለቅቱ ከተማ አስተዳደር ነው የ2015 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር በይፋ የተጀመረው።

በመርሃ ግብሩ የተገኙ የዞኑ ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ እና የመምሪያው ኃላፊ ተወካይ አቶ ዳንኤል ታደሰ በዞን ደረጃ በ2015 ዓ.ም በወጣቶች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባራት ላይ 234 ሺህ 1 መቶ በላይ ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን በፕሮግራሙ 662 ሺህ ህዝብ በላይ ተጠቃሚ እንድሆን እና ከመንግስት ካዝና ይወጣ የነበረውን ከ182 ሚሊዮን ብር በላይ ለማስቀረት ኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል ።

በተለይም በትምህርት፣ በጤና፣ የአቅመ ደካሞችንና የአረጋውያንን ቤት በማደስና የአረንጓዴ አሻራን ጨምሮ በአጠቃላይ በተመረጡ አስራ አምስት በተለያዩ ዘርፎች ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራና በዚህም መላው የዞኑ ህዝብም ሆነ የጨለለቅቱ ከተማ ማህበረሰብ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ባለፉት በበጋ ወራት በወጣቶች በጎ አገልግሎት በተከናወኑ ተግባራት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የጨለለቅቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተስፋዬ ፈይሳ ተናገረዋል።

ከንቲባው አክለውም በከተማ አስተዳደሩ ዘንድሮ በወጣቶች የክረምት በጎ አገልግሎት ተግባር አጠቃላይ 3400 ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን 11ሺህ 1 መቶ 53 የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑና ከመንግስት ካዝና ይወጣ የነበረውን 2 ሚሊዮን 560 ሺህ ብር ወጪ ለማስቀረት ግብ ጥለው ወደ ተግባር መግባታቸውን ገልጸዋል ።

የከተማው ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ህዝቅኤል ተሰማ በበኩላቸው ሥራዎች እየተሠሩ ያሉበት ሁኔታ በከተማው ከተዋቀረው አአብይ ኮሚቴ፣ ከጽ/ቤቱ ባለሙያዎች እና ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በመርሀ ግብሩ ለተሳተፉ ወጣቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል።

በመርሀ ግብሩ የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ለምለም ከበደን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የከተማው ወጣቶች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ዘጋቢ ፡ እንግዳየሁ ቆሳ ከፍስሃ ገነት ጣቢያችን