7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ነፃና ገለልተኛ በመሆኑ ውጤትን በፀጋ መቀበል ያስፈልጋል ሲሉ የዲላ ከተማ መራጮች ተናገሩ
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በወናጎ ምርጫ ክልል ሁለት የተለያዩ ጣቢያዎች የድምፅ ውጤት ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
በስፍራው ተገኝተን ያነጋገርናቸው የዲላ ከተማ ነዋሪዎች፤ ምርጫው ሰላምና ዲሞክራሲ የተንፀባረቀበት እንደነበር በመግለፅ ከዚህ ቀደም ከነበረው ለየት እንደሚልም ተናግረዋል።
አቶ ሙህዲን ረዲና ቶፊቅ ኑረዲን የዲላ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ ምርጫው ሰላማዊና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ በጥሩ ሁኔታ መካሄዱን ጠቅሰው የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ነፃና ገለልተኛ እንደነበር አስረድተዋል።
ጠቅላላ ምርጫውን ነፃና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ መምረጣቸውን የተናገሩት ወ/ሮ ዘርፌ ደሳለኝ እና አቶ አለማየሁ መኮንን፤ ይሆነኛል ያሉትን በመምረጥ መጠናቀቁን አንስተው ጊዚያዊ ውጤቱንም በማየታቸው መደሰታቸውንም ተናግረዋል።
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ነፃና ገለልተኛ እንደነበር በመጥቀስ የዘንድሮው ምርጫ ከዚህ ቀደሙ ለየት ያለ እንደሆነ አንስተው ውጤትን በፀጋ መቀበል እንደሚገባም ገልጸዋል።
ዘጋቢ: ውብሸት ካሳሁን – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ነፃና ገለልተኛ በመሆኑ ውጤትን በፀጋ መቀበል ያስፈልጋል ሲሉ የዲላ ከተማ መራጮች ተናገሩ

More Stories
በክልሉ በ2018 በጀት አመት ከ336 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ከምዝበራና ከብክነት ማዳን መቻሉ ተገለጸ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈፀሚያ ከ45.7 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አፀደቀ
“አንድነት የሚገነባው በውይይት ነው፤ ሰላም የሚጠናከረው በመግባባት ነው” ኢማም ሐጂ አብዱልሃዲ ሼክ አህመድ ቡርሃን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት