“ምርጫው በሠላም በመጠናቀቁ ተደስተናል” – የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሠላማዊ መንገድ በመካሄዱ መደሰታቸውን የቦንጋ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
አቶ ዮሴፍ ስለሺ፣ አቶ ታየ ገብረማርያም፣ ወ/ሮ ምህረት ይስሃቅ እና አቶ ምስክር ዘለቀ
በሰጡት አስተያየት፤ ምርጫው በሠላማዊ መንገድ መከናወኑን ተናግረዋል።
በምርጫ ቦርድ የሰዓት ጭማሪ ምክንያት እስከ እኩለ ለሊት ድረስ ሥርዓት ባለው መንገድ መምረጣቸውን አስታውቀዋል።
የምርጫ ቦርድ ሰራተኞች፣ የፀጥታ አካላት፣ የምርጫ ታዛቢዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ተወጥተዋል ነው ያሉት።
የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ለአቅመ-ደካሞችና ለአካል ጉዳተኞች ቅድሚያ ተሰጥቶ መከናወኑን ጠቁመዋል።
በቦንጋ ከተማ አስተዳደር በአብዛኞቹ ምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራ ስራ እየተከናወነ ይገኛል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ተመራጮችና መራጩ ህዝብ የምርጫው ጊዜያዊ ውጤት ይፋ እስኪሆን በትዕግስት መጠባበቅና ሲገለፅም በፀጋ መቀበል እንዳለባቸው አስተያየት ሰጥተዋል።
ዘጋቢ፡ ዮሐንስ ክፍሌ – ከቦንጋ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው