የተርጫን ለኑሮ ምቹና ተመራጭ እንድትሆን ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወናቸው የተሻለ ለውጥ እየታየ ነው – የከተማዋ አስተዳደር ከንቲባ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 11/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የተርጫ ከተማን ለኑሮ ምቹና ተመራጭ እንድትሆን ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወናቸው የተሻለ ለውጥ እየታየ መምጣቱን የከተማዋ አስተዳደር ከንቲባ ገለፁ፡፡
ካለፉት ዓመታት ይልቅ አሁን በመሠረተ ልማት ዝርጋታ መሻሻሎች መኖራቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
በመንግሥትና በኅብረተሰብ ተሳትፎ እየተገነቡ የሚገኙት የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎችን የከተማው ነዋሪዎች በመጠበቅ እና በመንከባከብ የድርሻቸውን መወጣት አለብን በማለት ነዋሪዎቿ ተናግረዋል፡፡
የተርጫ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ባቲሣ ወንድሙ እንደሚሉት በከተማዋ የነዋሪዎቿን የልማት ፍላጎት ለመመለስና የመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ጥያቄን ለመመለስ የሚያስችል ሥራ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል፡፡
በተለይም ከከተማዋ ዕድገት ጋር ተያይዞ የሚታየውን ፈጣን ለውጥ አጠናክሮ ለማስኬድ የነዋሪዎቿ ብርቱ ጥረት እንደሚፈልግም አቶ ባቲሣ አሳስበዋል፡፡
የታርጫ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳዊት በበኩላቸው በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ለመንገድ ከፈታና ጠጠር ማልበሻ፣ ለጎርፍ መውረጃና ፍሳሽ ማሰወገጃ ቦይ ግንባታ፣ ለመንገድ ዳር መብራት ዝርጋታ፣ የአረጋውያን መኖሪያ ግንባታ እና መሠል የልማት ተግባራት ከ34 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የልማት ተግባራቱ እየተከናወኑ መገኘታቸውን አስረድተዋል፡፡
በፌዴራልና በክልል መንግሥታት ወጪ ከ2 መቶ 15 ሚሊዮን ብር በላይ እየተገነባ የሚገኘው የንጹሕ መጠጥ ውሃ ግንባታና ዝርጋታ በተያዘለት የጊዜ ገደብን እንዲጠናቀቅ የሚያስችሉ የድጋፍ ሥራዎችም እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡
መሣይ መሰለ ከዋካ ቅርንጫፍ
More Stories
“አንድነታችንን በማጎልበት የህዝብ ጥቅም የሚያስቀድም ፖለቲካ ማራመድ ይጠበቅብናል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት መጠናከር መሰረት የሆነው ብዝሃነትን በአግባቡ የማስተናገድ ሂደት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገለፀ
በክረምቱ ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ