የሀዲያ ዞን ትምህርት ቤቶችን መሠረተ-ልማት ለማሻሻል የተዘጋጀ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 11/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሀዲያ ዞን ትምህርት ቤቶችን መሠረተ-ልማት ለማሻሻል የተዘጋጀ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በዞኑ የኢንስፔክሽን አገልግሎት ካገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል 87 ከመቶ እንዲሁም ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል 60 ነጥብ 6 በአጠቃላይ 83 ነጥብ 6 ከመቶ ትምህርት ቤቶች በትምህርት መሠረተ-ልማት ግብዓት ከደረጃ በታች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ትኩረት ያደረገ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ነው እያተካሄደ የሚገኘው።
መድረኩም “ትምህርት ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ሲሆን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም መጫን ጨምሮ ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተሳትፏል።
ዘጋቢ፡ አለቃል ደስታ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ውድና ውስን የሆነውን መሬት ያለብክነት ለመምራትና ለመጠቀም እየተሰራ ነው – የባስኬቶ ዞን አስተዳደር
በጎፋ ዞን ጋልማ ከተማ በ2019 በጀት ዓመት ከ18 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱ ተገለፀ
የሀድያ ብሔር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓልን ለማክበር በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ