ሀዋሳ፡ ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የአረንጓዴ አሻራ ልማት የኢትዮጵያን የውስጥ አንድነት ያጠናከረ ነው ሲሉ የደቡብ ክልል መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጥላሁን ከበደ ተናገሩ።
በአንድ ጀምበር የተከናወነው የ5 መቶ ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን ገፅታ ለአለም ህዝቦች ያሳየ መሆኑም ተጠቁሟል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር 5 መቶ ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተከናውኗል።
የኢትዮጵያ የአሩንጓዴ አሻራ ልማት ለአገር ዕድገት መሰረት በመጣል የህዝቦችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጠና የኢትዮጵያን የውስጥ አንድነት ያጠናከረ ነው ሲሉ የደቡብ ክልል መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጥላሁን ከበደ በሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ የአረንጓዴ አሻራቸውን ባሳረፉበት ወቅት ተናግረዋል።
በመላ ሀገሪቱ በአንድ ጀምበር የተከናወነው የ5 መቶ ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን ገፅታ ለዓለም ህዝቦች ያሳየ ኢኮኖሚያዊ ትስስርንም የሚያጠናክር ታሪካዊ ቀን ነው ያሉት ደግሞ የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚንስትር አቶ ቀጅላ መርዳሳ ናቸው።
የአሩንጓዴ አሻራ ከአካባቢና አየር ንብረት ለውጥ ባሻገር የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ለወጣቱ የሐብትና የስራ ዕድል መፍጠሪያም ጭምር መሆኑን ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ቴዎድሮስ ወርቅነህ
More Stories
በክረምት የተከናወኑ የወጣቶች በጎ ተግባራት ከ180 ሚሊየን ብር በላይ ከመንግስት ሊወጣ የነበረ ወጪ ማዳን መቻሉ ተገለጸ
የችሎት መዝገብ ስራ በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ የደንበኞቹን እርካታ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለፀ
የፀጥታና የደህንነት ስጋቶችን በጋራ በመታገል ለሁለንተናዊ የሀገሪቱ ሠላም በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ ገለፁ