ነገ ለሚተከለው አንድ ቀን አረንዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ማለዳ በነቂስ ወጥተው ለመትከል መዘጋጀታቸውን የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ገለፁ

ነገ ለሚተከለው አንድ ቀን አረንዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ማለዳ በነቂስ ወጥተው ለመትከል መዘጋጀታቸውን የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ገለፁ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ነገ ለሚተከለው አንድ ቀን አረንዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ማለዳ በነቂስ ወጥተው ለመትከል መዘጋጀታቸውን የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ነዋሪዎች ችግኞችን ተከላ ወደሚካሄድባቸው ቦታዎች የማጓጓዝ ሥራ እያጠናቀቁ ስለመሆናቸው ገለፀው ማለዳ 12፡00 ሰዓት ላይ   ወጥተው እንደሚተክሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ታሪካዊ በሆነው ኢትዮጵያን እናልብሳት መርሐ ግብር ስለምንሳተፍ ደስተኞች ነን ያሉት አስተያየት ሰጪዎች የሚተከሉ ችግኞች ዘርፈብዙ ጠቀሜታው ያላቸው በመሆናቸው የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና የኢኮኖሚ አቅምን ለማሳደግ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ነው ብለዋል።

ለተከላ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን በመያዝ ለመርሐ ግብሩ ያመች ዘንድ በአደረጃጀት ተለይታው እንደሚወጡም ነዋሪዎች ገልፀው መላው ኢትዮጵያዊያን ቃላችን ጠብቀን አሻራችንን እናሳርፍ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በደቡብ ኦሞ ዞን ነገ በአንድ ቀን ጀምበር 9 መቶ 13 ሺህ 46 ችግኞች በዞኑ በ10 ወረዳዎችና በሦስት ከተማ አስተዳድሮች ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል።

የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ጂንካ ቅርንጫፍ በወረዳዎች ተንቀሳቅሶ የችግኝ ዝግጅትና ለተከላው የተዘጋጁ ጉድጓዶችን ቅኝት አድርጓል።

ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን