በጉራጌ ዞን ከ175 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ

በጉራጌ ዞን ከ175 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በጉራጌ ዞን እምድብር ከተማ ከ175 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በክልሉ መንግስት እና በ“ዋንወሽ” የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የደቡብ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በተገኙበት ተመርቋል።

የንጹህ መጠጥ ውሃው ከ35 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

የንጹህ መጠጥ ውሃ ተገንብቶ መጠናቀቅ የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሚናው የጎላ ነው።

በውሃ ምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የደቡብ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳውን ጨምሮ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ግርማ፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የከተማው አመራሮች፣ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ ፡ የጉራጌ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ