ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በወልቂጤ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው
ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 13/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በወልቂጤ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ይገኛል።
በድጋፍ ሰልፉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ የክልሉ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ፣ በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገብረ መስቀል፣ የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ አሚን በደዊ፣ የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ ሙራድ ከድር፣ የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ካሱ ጁሀርን ጨምሮ የብልጽግና ፓርቲ አባላት እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
“ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሔደ ባለው የድጋፍ ሰልፍ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ተካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ “ምርጫዬ ብልጽግና ነው”፣ “ትላንትን ማከም ነገን መተለም”፣ “የጸና ሰላም የተቃና ስርዓት” የሚሉ እና ሌሎችም መፈክሮች ተስተጋብተዋል።
ዘጋቢ፡ ሪድዋን ሰፋ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው