በቤንች ሸኮ ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዬን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 43 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደስራ መግባታቸው ተገለፀ

በቤንች ሸኮ ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዬን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 43 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደስራ መግባታቸው ተገለፀ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 05/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ)በቤንች ሸኮ ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዬን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 43 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ተቀብሎ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ማሰማራት መቻሉን የዞኑ ንግድና ኢንቨስትመንት መምሪያ አስታውቋል ።

ፕሮጀክቶቹ ከ1 ሺህ 560 በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የስራ ዕድል መፍጠር ችለዋል

በመምሪያው የኢንቨስትመንት ፖቴንሺያል ጥናት ፕሮሞሺን ፍቃድና መረጃ ቡድን መሪ አቶ ተስፋዬ ዳባ እንደተናገሩት በዞኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዬን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 43 ባለሀብቶች ተቀብሎ በተለያየ የኢንቨስትመንት ስራ ዘርፎች ማሰማራት መቻሉንተናግረዋል

በዞኑ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ወስደው ወደስራ የገቡት እነዚህ ፕሮጀክቶች 10 በግብርና 27 በኢንዱስትሪና 5 በአገልግሎት ዘርፍ መሆናቸውንም አቶ ተስፋዬ አብራርተዋል

እነዚህም ፕሮጀክቶች በዞኑ ለሚኙ ከ1 ሺህ 562 ዜጐች ቋሚና ጊዜዊ የስራ እድል መፍጠር ችሏል ብለዋል፡፡

ዘጋቢ ፡ ጦያር ይማም ከሚዛን ጣቢያ