የቡሌ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት 26ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ
በውይይቱ ከምክርቤቱ አባላት ወ/ሮ መብራቴ በየነና አቶ ሀይሉ ኢርባ የህዝብ እንደራሴ የሆነው ምክር ቤት በዓመት ውስጥ በዕቅድ በተቀመጠው መሰረት ጉባኤ በማካሄድ የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ መመለስ ሲገባ ወደኋላ መቅረት ይስተዋላል ብለዋል።
የምክር ቤቱ አባላት አክለውምበመንገድ፣ ውሃ፣ የምክርቤት ህንጻ ግንባታና ተጀምሮ በቆመው የቡሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ዙሪያ ለምክርቤቱ ጥያቄ አንስተዋል።
የቡሌ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ዋቆ ሞኮና የህብረተሰቡ የረዥም ግዜ ጥያቄ የነበረው የቡሌ ከተማ አስተዳደር ማስተር ፕላን በክልል ምክር ቤት የጸደቀውን ለምክር ቤቱ አባላት በባለሙያ ገለጻ ከተደረገበት በኋላ እንዲጸድቅ መደረጉን ዋና አፈጉባኤው ተናግረዋል።
የህብረተሰብ ጥያቄ የሆነው በመንገድ፣ ውሃ፣ የምክር ቤት ህንጻ ግንባታና ተጀምሮ በቆመው የቡሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ዙሪያ ከወረዳው አስተዳዳሪ አቶ በራቆ በራሶ ምላሽ ተሰጥቶበታል።
የምክር ቤት ጉባኤ በዓመት ውስጥ መካሄድ የነበረበትን ያህል አልተካሄደም በሚል ከአባላቱ የቀረበው ቅሬታ ልክ ነው ያሉት የቡሌ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤው በዓመት ውስጥ 75 በመቶ ብቻ ጉባኤ ማካሄዳቸውን ተናግረዋል።
የህብረተሰቡ የረዥም ግዜ ጥያቄ የነበረው የቡሌ ከተማ አስተዳደር ማስተር ፕላን በክልል ምክር ቤት የጸደቀውን ለምክር ቤቱ አባላት በባለሙያ ገለጻ ከተደረገበት በኋላ እንዲጸድቅ መደረጉን ዋና አፈጉባኤው ተናግረዋል።
የህብረተሰብ ጥያቄ የሆነው በመንገድ፣ ውሃ፣ የምክር ቤት ህንጻ ግንባታና ተጀምሮ በቆመው የቡሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ዙሪያ ከወረዳው አስተዳዳሪ አቶ በራቆ በራሶ ምላሽ ተሰጥቶበታል።
ዘጋቢ ፡ ውብሸት ካሣሁን ከፍስሐገነት ጣቢያችን
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ