የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ለማሻሻል የተዘጋጀ የትምህርት ተሃድሶ ንቅናቄ እየተካሄደ ነው

የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ለማሻሻል የተዘጋጀ የትምህርት ተሃድሶ ንቅናቄ እየተካሄደ ነው

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 03/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ “ትምህርት ለትውልድ” በሚል መሪ ቃል የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ለማሻሻል የተዘጋጀ የትምህርት ተሃድሶ ንቅናቄ በሀዋሳ እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ በኢፌዴሪ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር በወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የሚመራው የሚኒስትሮችና የሚኒስትር ዴኤታዎች ልዑክ፣ የሲዳማ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በየነ በራሳ፣ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ መገኘታቸውን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።