ኢትዮጵያውያንን የሚያቀራርብ ስራ በትምህርቱ ዘርፍ እየተሰራ ነው – የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 01/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ኢትዮጵያውያንን የሚያቀራርብ ስራ በትምህርቱ ዘርፍ እየተሰራ እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ።
ከሁሉም የሃገሪቱ አካባቢ የመጡ ተማሪዎችን ማስተማር የሚችሉ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እያስገነባ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ትውልዱ ቀጣይቷን ኢትዮጵያ በጋራ እንዲገነባ ያስችላል ብለዋል።
በክልሉ ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች ናቸው ያሉት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ በመንግስትም ይሁን በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚገነቡ ትምህርት ቤቶች አጋዥ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የቡኢ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ መሰረተ ድንጋይ በዛሬው ዕለት በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ተቀምጧል።
የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ እና የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው የመሠረተ ድንጋዩን ያስቀመጡት።
አዳሪ ትምህርት ቤቱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ከሁሉም የሃገሪቱ አቅጣጫ የመጡ ተማሪዎች ይስተናገዳሉ ተብሏል።
አዳሪ ትምህርት ቤቱ በሃገር አቀፍ ደረጃ ከሚገነቡ ሃምሣ አዳሪ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ ነው።
የቡኢ አዳሪ ትምህርት ቤት በ2017 ዓም. ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሏል።
ትምህርት ቤቶችን መልሶ የመገንባትና የማደስ ንቅናቄ እንደ ደቡብ ክልል በቡኢ ተካሂዷል።
ዘጋቢ: ሲሳይ ደበበ
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ