ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ፡-
የግሉን ዘርፍ ለማነቃቃት መንግሥት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን፤
በማይክሮ ኢኮኖሚ ዘርፍ የተከሰተውን ስብራት ለመጠገን መንግሥት ከፍተኛ ስራ እየሰራ መሆኑን፣
ሁለተኛው ዙር ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዕቅድ መዘጋጀቱንና የተዘጋጀው ዕቅድ እየታዩ ያሉ ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ እንደሚታመን፣
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ባወጣው መረጃ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አምና 6.4 በመቶ፣ ዘንድሮ 6.1 በመቶ፣ በቀጣይ አመት ደግሞ 6.4 በመቶ ያድጋል በሚል የተነበየ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ 7.5 በመቶ ዕድገት እንደሚጠብቅ፣
ግብርና 6.3 በመቶ፣ ኢንዱስትሪ 8.2 በመቶ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፍ 7.5 እድገት ያሳዩ መሆኑን፣
160 የሚሆኑ የማምረቻ ፋብሪካዎች ወደ ሙሉ አቅም ማምረት መሸጋገራቸው የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ትልቅ ሚና መጫወታቸውን፣
ዜጎችን እየፈተነ ያለውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠር መንግስት ገበያው ውስጥ ከመጠን በላይ የተሰራጨውን ገንዘብ ለመሰብሰብ እየሰራ መሆኑን፣
የዋጋ ግሽበት ዓለም አቀፍ ችግር መሆኑንና ኢትዮጵያም የዚህ ገፈት ቀማሽ ስለመሆኗ፣
ከለውጡ በፊት የኢትዮጵያ GDP 2.2 ትሪሊዮን ብር ብቻ እንደነበረ እና አሁን ላይ 6.2 ትሪሊዮን ብር ስለመድረሱ አንስተዋል፣
More Stories
በዕቅድ የሚመራ የመፈፀም አቅሙ ያደገ ሲቪል ሰርቫንት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን በደቡብ ኦሞ ዞን የሳላማጎ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ገለፀ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከውጭ ይገቡ የነበሩትን ሰብሎች በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየተሰራ ያለው ስራ ውጤታማ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰመስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው አስታወቁ
የፖሊስ አባላትና ሲቪል ሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ