በቤንች ሸኮ ዞን ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 27/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በቤንች ሸኮ ዞን ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።
የቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ግዛው ሀይሌ እንደተናገሩት፥ በዞኑ ከትላንት ጀምሮ ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ያለምንም ችግር በሰላም መጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡
ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች ሰፊ መሆናቸውን ተከትሎ በፈተና ጣቢያዎች ላይ የተቀመጡ አዳዲስ አሰራሮችና የተደረጉ ክልከላዎች ለፈተናው ስኬታማነት አጋዥ ነበሩ ብለዋል።
ከዚህ በተጓዳኝ በየደረጃው የሚገኙ የፀጥታና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ አቶ ግዛው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በዞኑ የሚገኙ ተማሪዎች ፈተናውን በተገቢው መንገድ አንብበውና ተረጋግተው የወሰዱ ሲሆን ከኩረጃ በፀዳ መልኩ መከናወኑንም ጠቁመዋል።
በዞኑ በ2015 ዓ.ም በ200 ፈተና ጣቢያዎች ላይ 11ሺህ 800 በላይ ተማሪዎች ክልላዊ ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ጦያር ይማም – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ
የይርጋጨፌ ከተማን የኮሪዴር ልማት ለነዋሪዎች ምቹ ከተማ እንዲትሆን ከማድረግ ባለፈ የከተማዋን ገፅታ የቀየረ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ
የፍትህ ሪፎርም ተግባራዊ በማድረግ በዘርፉ እየታዩ ያሉ ማነቆዎችን ማረም እንደሚገባ ተገለፀ