አካል ጉዳተኛ ህጻናትን በማገዝ የተሻለ የነገ ህይወት እንዲኖሩ ብርሃን ለህፃናት ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር ሥራዎች መጀመሩን አስታውቋል።
የጉራጌ ህዝብ ራስ አገዝ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ መቻል አወርቃ እንደገለፁት፤ ድርጅቱ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ሲሰራ ቆይቷል።
የህፃናት ፓርላማዎችን በማቋቋምና በተለያዩ ዘርፎች የበቁ ወጣቶችን ማፍራታቸውን ገልፀው በአካል ጉዳተኛ ህፃናት ላይ ብርሃን ለሕፃናት ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር ለመስራት ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።
በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ሁለት ትምህርት ቤቶች የአካል ድጋፍ ለማድረግ፣ የመምህራን ስልጠና ለመስጠት፣ የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግና መፀዳጃ ቤቶችን ምቹ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
የብርሃን ለህፃናት ድርጅት መስራችና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ እቴነሽ ወንድምአገኘሁ በበኩላቸው፤ ከ30 አመት በፊት አዲስ አበባ ከተማ በ6 ቀበሌዎች በ265 አካል ጉዳተኛ ህፃናት ስራ መጀመሩን አስታወሰው ህፃናቱን በማገዝ ያላቸውን ችሎታ አጎልብቶ ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
አካል ጉዳተኛ ህጻናትን ማገዝ የተሻለ የነገ ህይወት እንዲኖራቸው ማገዝ በመሆኑ ከመንግሥት፣ ከለጋሽ ድርጅቶችና ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰሩ መሆኑን ጠቁመው የአካል ድጋፍ፣ የትምህርት እድል፣ የግንዛቤ ማስጨበጫዎችና ሌሎችም እገዛዎች እንደሚደረጉ አስረድተዋል።
እስከ ዛሬ ድረስ 18 ሺ ለሚበልጡ ሁሉም አይነት አካል ጉዳተኛ ህፃናት ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አክለዋል።
የተቀናጀ የተሀድሶ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን የገለፁት ወ/ሮ እቴነሽ፤ በአሁኑ ሰአት በ5 ክልሎች ላይ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ከጉራጌ ህዝብ ራስ አገዝ ልማት ድርጅት ጋር መስራት መጀመራቸውን ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ ሄኖክ ተክሌ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
5ኛው አገራዊ የሠላም ኮንፈረንስን በተመለከተ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት የኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተላለፈ መልዕክት
ፈጣን ፣ ወቅታዊ እና ተአማኒ መረጃን ተደራሽ ለማድረግ ዘመኑን የሚመጥን አሰራርን መዘርጋት እንደሚገባ ተገለጸ
በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በ15 መስኮች በተከናወኑ ተግባራት ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን መቻሉ ተገለጸ