ፈጣን ፣ ወቅታዊ እና ተአማኒ መረጃን ተደራሽ ለማድረግ ዘመኑን የሚመጥን አሰራርን መዘርጋት እንደሚገባ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 01/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ፈጣን ፣ ወቅታዊ እና ተአማኒ መረጃን ተደራሽ ለማድረግ ዘመኑን የሚመጥን አሰራርን መዘርጋት እንደሚገባ በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የአርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገለፀ።

‎ድርጅቱ እድሳት የተደረገለትን ዘመናዊ ስቲዲዮ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል።

‎ለድርጅቱ ጋዜጠኞች እና ሰራተኞች አዲሱ የዲሲፕሊን አፈፃፀም መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል ።

‎ሰኔ 1 ቀን 2001 ዓ.ም የተመሰረተው የህብረ ብሔራዊነት ድምፅ የሆነው በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አርባምንጭ ቅ/ፍ ኤፍ ኤም 90.9 ሬዲዮ÷ ለ 17 ተከታታይ ዓመታት ከዋናው ማዕከል ደቡብ ኤፍ ኤም 100.9 ስርጭትን በሊንክ ተቀብሎ ከማሰራጨት በተጨማሪ በአከአባቢው በሚገኙ ሶስት ዞን ውስጥ የሚኖሩ 8 ብሔረሰብ ቋንቋዎችን መረጃ ተደራሽ ሲያደርግ መቆየቱ ተመላክቷል፡፡

‎ድርጅቱ አሰራሩን ለማዘመንና ተደራሽነቱን ለማሳደግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የሚታይና ተጨባጭ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን÷ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ድርጅቱ ተወዳዳሪ እንዲሆን ከተባባሪ ድርጅቶች ጋር በሚሰሩ የሪፎርም ተግባራት በጋዜጠኛውና አመራሩ ላይ መነቃቃትን ፈጥረዋል።

‎ድርጅቱ በአዲስ መልክ ያሳደሰውን ዘመናዊ ስቱዲዮ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሲያደርግ÷ የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የጀመራቸውን የሪፎርም ሥራዎችን የሚያግዙ የሠራተኛ መተዳደሪያ ደንብ እና የዲስፒሊን አፈጻጸም መመሪያ ከማዕከል የመጡ ከፍተኛ የሰው ሐብት ባሙያዎች ለሠራተኛው ስልጠና ሰጥተዋል።

‎ድርጅቱ ከባህላዊ አስተሳሰብ፣ አመለካከት እንዲሁም አሰራር በመውጣት ፈጣንና ወቅታዊ መረጃን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ለጀመራቸው ተግባራት የሚዲያ ሠራተኞች ቁርጠኛ መሆን እንዳለባቸው የማዕከሉ የሰው ሀብት ስራ አመራር ዳይሮክተሬት የሰው ሐብት ቡድን መሪ አቶ ኃይሉ መኩሪያ እና ከፍተኛ ባለሚያ አቶ ብርሀኑ ኃ/ሚካኤል አብራርተዋል ።

‎በመርሀ ግብሩ የዋናው ድርጅት የሰው ሀብት አስተዳደር ባለሙያዎችን ጨምሮ የአርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሥራ ሀላፊዎች እና የተቋሙ ሠራተኞች ታድመዋል።

ዘጋቢ: ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን