ግራሃም ፖተር የሲዊዲን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን ተሾሙ

ግራሃም ፖተር የሲዊዲን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን ተሾሙ

የቀድሞ የቼልሲ አሰልጣኝ ግራሃም ፖተር የስዊድን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን ተሹመዋል።

ከ24 ቀናት በፊት ከዌስትሃም ሀላፊነታቸው የተሰናበቱት እንግሊዛዊው አሰልጣኝ በአጭር ጊዜ ኮንትራት የባልካን ሀገሯን በሀላፊነት መረከባቸውን ዘጋርዲያን አስነብቧል።

የ50 ዓመቱ አሰልጣኝ ስዊድንን ወደ ዓለም ዋንጫ የማሳለፍ ሀላፊነት እንደተጣለባቸው ተገልጿል።

ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ