በደቡብ ኦሞ ዞን አራት ወረዳዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለተከሰተው የምግብ እጥረት የሰብአዊ ድጋፍ የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 22/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በደቡብ ኦሞ ዞን አራት ወረዳዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለተከሰተው የምግብ እጥረት የሰብአዊ ድጋፍ የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አካሂዷል።
ድጋፍ የሚደረግላቸው ዳሰነች፣ ሐመር፣ ኛንጋቶም እና ሰላማጎ ወረዳዎች ሲሆኑ ድጋፉ ከ259 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሆነ በመርሃ-ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ተገልጿል።
ድጋፉ የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ ካለበት መሰረታዊ ችግር እንዲወጣ ለማድረግ ያለመ ስለመሆኑ ተጠቁሟል።
በሚደረገው የሰብዓዊ እርዳታ በአራቱም ወረዳዎች ከ140 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ታውቋል።
በመርሃ-ግብሩ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የአመራር አካላትን ጨምሮ የደቡብ ክልልና የዞኑ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ወንድወሰን ሽመል ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ጉልህ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ