ለአገረ መንግሥት ግንባታ ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት የወል እውነቶችን በማጽናት ለጋራ ተጠቃሚነት ትግል ማድረግ  የአመራሩ ቀዳሚ አጀንዳ መሆን አለበት – አቶ አልማው ዘውዴ

ለአገረ መንግሥት ግንባታ ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት የወል እውነቶችን በማጽናት ለጋራ ተጠቃሚነት ትግል ማድረግ  የአመራሩ ቀዳሚ አጀንዳ መሆን አለበት – አቶ አልማው ዘውዴ

ሀዋሳ፡ ሰኔ 17/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ለአገረ መንግሥት ግንባታ ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት የወል እውነቶችን በማጽናት ለጋራ ተጠቃሚነት ትግል ማድረግ የአመራሩ ቀዳሚ አጀንዳ መሆን እንዳለበት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ ተናገሩ፡፡

በዳዉሮ ዞን ለሚገኙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች “መፍጠንና መፍጠር” የወል እውነቶችን የማጽናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሥልጠና መሰጠት ተጀምሯል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በሥልጠናው መክፈቻ እንደተናገሩት ከዚህ ሥልጠና የፖለቲካ አቅም በመፍጠር ለቀጣይ የብልጽግና ጉዞ ዝግጁነት እና ተነሳሽነትን ከፍ ለማድረግ የሚያስችል ነው።

አሁን ላይ አገራዊ ለውጥን መነሻ በማድረግ የፖለቲካ እና የነባራዊ ሁኔታ ግልጸኝነት በመያዝ ወደ ተግባር ለመግባት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ለውጤታማነት ትግል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በቀጣይም የአገረ መንግሥት ግንባታ ላይ ወቅታዊ፣ ቀጠናዊ፣ አገር እና አለምአቀፋዊ ኩነቶችን በመረዳት የብልጽግና ጉዞን በሚፈለገው መንገድ እውን ለማድረግና ለማሣካት እንዲቻል የአቅም ግንባታ በመፍጠር፣ አመራሩ ለመፍጠርና ለመፍጠን እንዲነሣሣ የሚያግዝ መሆኑንም አቶ አልማው ዘውዴ ተናግረዋል።

የብልጽግናን ጉዞ ለማሣካት የአመራር እይታ ለውጥ በማድረግ፣ የተግዳሮትንና የስኬት  ሚዛናዊነትን አስጠብቆ ወደ ተግባር ለመግባት የትግልና የፖለቲካ አውድ ግልጽ የሆነ ግንዛቤ በመፍጠር፣ ለውጤትና ለለውጥ መፍጠን አስፈላጊ መሆኑንም አብራርተዋል።

ለአገረ መንግሥት ግንባታ ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት የወል እውነቶችን በማጽናት ለጋራ ተጠቃሚነት ትግል ማድረግን  የአመራሩ ቀዳሚ አጀንዳ መሆን እንዳለበትም ገልጸዋል።

እስካሁን በአገር ደረጃ በብዝሃ ኢኮኖሚ የተመዘገቡ ከፍተኛ ምርታማነት፣ የተቋማት ግንባታ እና ሕልውናን ማስቀጠል የተገኙ ዋና ዋና ስኬቶች መሆናቸውን የገለጹት ሲሆን ካጋጠሙ ፈተናዎች መካከል የዋጋ ንረት፣ የሰላም እጦትና ያለመረጋጋት፣ የሥራ አጥነት ችግርና ተለዋዋጭ የሆነ  የዓለም ሁኔታ ተጠቃሽ መሆናቸውንም አስረድተዋል።

ስለሆነም የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞን በስፋት፣ በጥልቀትና በፍጥነት አጠናክሮ በማስቀጠል የዜጎችን ፍላጎት ለማሟላት አመራሩና አባሉ በትኩረት ተግባራትን ማከናወን እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

በሥልጠናው የተገኙ የዳዉሮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ በበኩላቸው ከዞኑ ማዕከላትና ከ10 ወረዳዎች እንዲሁም ከሁለቱ የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች የተገኙ አመራሮች ሥልጠናውን በቁርጠኝነትና በዲስፕሊን መከታተል እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በሥልጠናው 4 መቶ 47 ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የሚሳተፉ ሲሆን ለሚቀጥሉ አራት ተከታታይ ቀናት በተርጫ ማዕከል የሚሰጥ ይሆናል።

ዘጋቢ፡ መሣይ መሠለ – ከዋካ ጣቢያችን