የፀጥታና የደህንነት ስጋቶችን በጋራ በመታገል ለሁለንተናዊ የሀገሪቱ ሠላም በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ ገለፁ
የቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት የግብ ስምምነት መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ፤ ዘላቂ ሠላምን በማጽናት የተረጋጋችና ልማቷ የተረጋገጠ ሀገር ለመፍጠር በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ አመላክተዋል።
ሠላም የጽናትና የመረጋጋት ውጤት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተመስገን፤ ሠላምን የሚያደናቅፉ ተግባራትን ህብረተሰቡም ሆነ ባለድርሻ አካላት በጋራ መታገል እንደሚኖርባቸው ገልፀዋል።
በክልላችን በአንዳንድ አካባቢዎች የሚከሰቱ የፀጥታና የደህንነት ስጋቶችን ለመታገል ከምን ጊዜውም በላይ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ጠቁመው ፤ ግጭት ከመፈጠሩ በፊት መከላከል ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህም ክልሉን የሠላም ተምሳሌት ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች አፈታትና የዜጎች ቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓት ትግበራ ዙሪያ ለሚመለከታቸው አካላት አቅም ማጎልበቻ ስልጠና እንደሚሰጥም አቶ ተመስገን ተናግረዋል።
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ በበኩላቸው፤ የታችኛው መዋቅር በክልሉ የሚቀመጡ የስራ አቅጣጫዎችን ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ጠቁመው የመረጃ ቅብብሎሽ ስርዓትም የተጠናከረ ሊሆን እንደሚገባ አመላክተዋል።
ማህበራዊ ሚዲያን ለተገቢ ሀገራዊ ገምቢ ዓላማ ብቻ መጠቀም ያስፈልጋል ያሉት ኮሚሽነሩ፤ የህግ የበላይነትን በጋራ ለማስከበር በጋራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡን አስተያየት፤ ሠላም የማናቸውም የልማት ተግባራት መሠረት መሆኑን በመጠቆም በክልሉ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ፀረ ሠላም አመለካከቶችን በጋራ መታገል የሚገባ መሆኑን አንስተዋል።
እንደ ተቋም ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የተሰራው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው በተለያዩ አካባቢዎች ፀረ ሠላም ኃይሎች መኖራቸውን ታሳቢ በማድረግ ህዝቡን የሠላምና ፀጥታ ባለቤት የማድረጉ ተግባር ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው ብለዋል።
ጉባኤው በክልሉ እስከታችኛው መዋቅር የሚገኙ የሠላምና ፀጥታ መዋቅር አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት “ዘላቂ ሠላም ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን በቅንጅት በመስራት ዘላቂነት ያለውን ሠላም ማስፈን በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በጥልቀት በመምከር ከጉባኤው ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በባለድርሻ አካላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
ዘጋቢ: አማኑኤል አጤቦ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
በክረምት የተከናወኑ የወጣቶች በጎ ተግባራት ከ180 ሚሊየን ብር በላይ ከመንግስት ሊወጣ የነበረ ወጪ ማዳን መቻሉ ተገለጸ
የችሎት መዝገብ ስራ በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ የደንበኞቹን እርካታ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለፀ
ተቋም የህግ ታራሚዎች የሰብዓዊ መብት አያይዝ የተሻለ መሆኑን የአሪ ዞን ፍትህ መምርያ አስታወቀ