ተቋም የህግ ታራሚዎች የሰብዓዊ መብት አያይዝ የተሻለ መሆኑን የአሪ ዞን ፍትህ መምርያ አስታወቀ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 05/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በጂንካ ማረምያ ተቋም የህግ ታራሚዎች የሰብዓዊ መብት አያይዝ የተሻለ መሆኑን የአሪ ዞን ፍትህ መምርያ ገለጸ፡፡
በማረምያ ተቋሙ በአስተሳሰብ የታነፁ አምራች ዜጎችን ለማፍራት ልዩ ትኩረት ተሠጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተመላክቷል፡፡
አስተያየታቸዉን ከሰጡን የህግ ታራሚዎች መካከል አበራ አባተ፣ አንዷለም ደላዉና ጋቲኝ አለማን በጋራ ሰብዓዊ መብታቸዉ ተከብሮ አምራችና ብቁ ዜጋ ሁነዉ ታንፀዉ ማህበረሰቡን እንዲቀላቀሉ ከተቋሙ ጋር ቤተሰባዊ ግንኙነት እንዳላቸዉ ተናግረዋል፡፡
በጂንካ ማረምያ ተቋም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መ/ርት ማርታ ሙላትና ር/መ/ር ቁምላቸዉ ሚናስ በጋራ በሰጡት አስተያየት፥ ታራሚዎች በትምህርት ቆይታቸው በቂ እዉቀትና ክህሎት አግኝተዉ፣ ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ ማረምያ ተቋሙ አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና የመማርያ መፀሐፍ በማቅረብ የመማር ማስተማር ስራዉ በወቅቱ መጀመሩን ገልጸዉ የላብራቶሪ አገልግሎት አለመኖር ለትምህርት ጥራት ማነቆ ነው ብለዋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ማረምያ ፖሊስ ኮምሺን የጂንካ ማረምያ ፖሊስ ተቋም አዛዥ ምክትል ኮማንደር አስቻለዉ ነሬሬ ታራሚዎች ሰብዓዊ መብታቸዉ ተከብሮ፣ በእዉቀት በልፅገዉ፣ አምራችና ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ ለማድረግ ከጎልማሶች ት/ት እስከ 12ኛ ክፍል የመማር ማስተማር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመው፥ ዩኒቨርስቲ የገቡ ታራሚዎች በመኖራቸዉ የላብራቶሪ አገልግሎት ለመስጠት ያለዉን የሰዉ ኃይል እጥረት ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር እተነጋገሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የጂንካ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዉባለም ገዛኸኝ፥ በከተማ አስተዳደሩ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመማር ማስተማር ስራዉ መጀመሩን ገልፀዉ በአስተሳሰብ የበለፀገ ዜጋ ማፍራት የጽ/ቤቱ ተግባር በመሆኑ ለማረምያ ተቋሙ በቂ ባይሆንም የሚመጡ የትምህርት ግበዓቶችን ቅድሚያ በመስጠት ተደራሽ እንደሚያደርጉና የላብራቶሪ አገልግሎቱንም ለማስጀመር የሰዉ ኃይል ቅጥር ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የአሪ ዞን ፍትህ መምርያ ኃላፊ አቶ ኤፍሬም ሙራ የማረምያ ተቋማት የታረሙና የታነፁ እንዲሁም አምራች ዜጋ የሚፈሩባቸዉ በመሆኑ የጂንካ ማረምያ ተቋም በህግ ታራሚዎች ሰብዓዊ መብት አያይዝ የተሻለ በመሆኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ካሉ ማረምያ ቤቶች በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል ፡፡
አዘጋጅ በናወርቅ መንግስቱ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
በክረምት የተከናወኑ የወጣቶች በጎ ተግባራት ከ180 ሚሊየን ብር በላይ ከመንግስት ሊወጣ የነበረ ወጪ ማዳን መቻሉ ተገለጸ
የችሎት መዝገብ ስራ በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ የደንበኞቹን እርካታ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለፀ
የፀጥታና የደህንነት ስጋቶችን በጋራ በመታገል ለሁለንተናዊ የሀገሪቱ ሠላም በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ ገለፁ