በጉራጌ ዞን ጠንካራ የጤና ልማት ስርአት በመዘርጋት የህብረተሰቡ የጤና አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለፁ።
የዞኑ ጤና መምረያ የ2017 በጀት አመት የጤና ስራዎች አፈፃፀም ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በጉባኤው ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በጉራጌ ዞን ጠንካራ የጤና ልማት ስርአት በመዘርጋት የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች የማህበረሰብ አቀፍ የመድሀኒት አገልግሎት መስጫ ተቀማትን በማቋቋም የመድሀኒት አቅርቦት ተደራሽነት ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ጠቁመው፥ የወባ በሽታን ለመከላከል በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት የማህበረሰቡን ግንዛቤ በማጎልበት ውጤታማ ተግባራት ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
በሽታን አስቀድሞ በመከለከሉ ረገድ በዞኑ ውጤታማ ተግባራት በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ያመላከቱት አቶ ላጫ፥ በዞኑ በየአካባቢው እየተሰሩ ያሉ ፅዱ መንደር የመፍጠር ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ አየለ ፈቀደ በበኩላቸው በዞኑ በ2017 በጀት አመት የህረተሰቡ ጤና የተጠበቀ እንዲሆን በየደጃው ከሚገኙ የጤና ተቋማትና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን አውስተዋል ።
የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ለማስፋት እና የወባ በሽታን ለመከለከል በተደረጉ ጥረቶች አመርቂ ውጤት መመዝገቡንና ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
በህክምና አገልግሎት በተለይም በማህፀን በር ጫፍ ካንሰር አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸውንና የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የተጠናከረ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።
በ2018 ለማከናወን የታቀዱ የጤና ስራዎች እንደየ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ በመፈፀም የህብረተሰቡ የጤና አገልግሎት ለማሻሻል በቅንጅት መስራት ያሻል ብለዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት እንደየወረዳቸው ተጨባጭ ሁኔት መንግስት ህብረተሰቡና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመቀናጀት ጤናው የተጠበቀ ህብረተሰብ ለመፍጠር ትኩረት ሰጥተው ሲሰሩ መቆየታቸውን አብራርተው በቀጣይም የዞኑን ማህበሰብ ጤና በማስጠበቅ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።
በዕለቱ በ2017 በጀት አመት የተሻለ ተግባር በመፈፀማቸው ዕውቅና የተሰጣቸው አካላት ባገኙት ዕውቅና መደሰታቸውን እና በቀጣይ የተሻለ የጤና ተግባር በመፈፀም የህብረተሰቡ ጤና ለመጠበቅ አቅደው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በመጨረሻም በ2018 በጀት አመት የጤና ስራ አፈፃፀም ላይ የዞኑ ጤና መምሪያ ከወረዳዎችና ከተማ አስተደደሮች ጋር የግብ ስምምነት ተፈራርሟል
ዘጋቢ፡ ፋአድ አብደላ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
በክረምት የተከናወኑ የወጣቶች በጎ ተግባራት ከ180 ሚሊየን ብር በላይ ከመንግስት ሊወጣ የነበረ ወጪ ማዳን መቻሉ ተገለጸ
የችሎት መዝገብ ስራ በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ የደንበኞቹን እርካታ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለፀ
የፀጥታና የደህንነት ስጋቶችን በጋራ በመታገል ለሁለንተናዊ የሀገሪቱ ሠላም በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ ገለፁ