አቶ ጌታቸው ኬኒ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሆነው ተሾሙ

አቶ ጌታቸው ኬኒ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሆነው ተሾሙ

የክልሉ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ አካሂዷል።

ምክር ቤቱ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤው ላይ የክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ አቶ ጌታቸው ኬንን ዋና አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ተወካይና ረዳት የመንግሥት ተጠሪ በአቶ በላይ ተሰማ አቅራቢነት አቶ ጌታቸው ኬኒ የክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሆነው እንዲሾሙ በምክር ቤት አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

በጉባኤው ላይ የክልሉ የመንግሥት ተወካዮች፣ የምክር ቤቱ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ: አስቻለው አየለ – ከማሻ ጣቢያችን