የዋካ ቅርንጫፍ ጣቢያ ወቅታዊና ጥራት ያለውን መረጃ ተደራሽ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በላቀ ደረጃ እንዲወጣ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

የዋካ ቅርንጫፍ ጣቢያ ወቅታዊና ጥራት ያለውን መረጃ ተደራሽ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በላቀ ደረጃ እንዲወጣ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ጣቢያው ወቅታዊና ጥራት ያለውን መረጃ ተደራሽ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በላቀ ደረጃ እንዲወጣ እየተሰራ መሆኑን በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የዋካ ቅርንጫፍ ጣቢያ ኤፍ.ኤም 93.4 አስታውቋል፡፡

የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እና የበጀት ዓመቱ ቀሪ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

የዋካ ቅርንጫፍ ጣቢያ በዳዉሮኛ፣ በወላይትኛና በኮንትኛ የብሔረሰብ ቋንቋዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ተቋሙ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት ባደረገበት ወቅት በወቅታዊ አገራዊና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች እንዲሁም በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ለአድማጮች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች መረጃ ሲያደርስ መቆየቱ ተገልጿል።

በተለያዩ የብሔረሰብ ቋንቋዎች የየብሔረሰቦቹን ወግ፣ ባህልና ቅርስ የሚያስተዋውቅ መሆኑም ተብራርቷል።

በተያዘው በበጀት ዓመትም ተደራሽነትን በማስፋት ወቅታዊና ጥራት ያለውን መረጃ ለማድረስ ጥረት እንደሚደረግ የዋካ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ወንድሙ ዋኮ ተናግረዋል።

ተቋሙ ከተቋቋመበት ዓላማ አንጻር በሦስቱ የብሔረሰብ ቋንቋዎች የሚዲያ ሽፋን ከመስጠት በተጨማሪ በእነዚህ አካባቢዎች የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን በደቡብ ቴሌቪዥን እና በደቡብ ሬዲዮ ኤፍ.ኤም 100.9 ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲተዋወቁ በማድረግ ተግባሩን በተገቢው እንደሚወጣ ገልጸዋል።

የተቋሙ ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት ባለፈው የበጀት ዓመት በጉድለት የተገመገሙ ነጥቦችን በማረም በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖር ለማስቻል የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡ መሳይ መሰለ – ከዋካ ጣቢያችን