ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን !
የመስቀል በዓል በታላቅ ኃይማኖታዊ ስርዓት ከሚከበሩ የአደባባይ በዓላት መካከል አንዱና በዓለም አቀፉ የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም /UNESCO/ በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ ልዩ በዓል ነው።
መስቀል በመደመር ዉስጥ ያለዉ ኃይልና ጉልበት የታየበት፣ በተለያዩ ባህሎችና ማህበረሰቦች ዉስጥ በድምቀት የሚከበር፤ ከኃይማኖታዊ ስርዓቱ በላይ የህብረ ብሄራዊ አንድነታችን መገለጫ የሆነ በዓል ነዉ።
በዓሉ ፍቅር የሚገለፅበትና አንድነት የሚያብብበት በዓል በመሆኑ በዓሉን ስናከብር እርስ በእርሳችን በመተሳሰብ፣ በመጠያየቅ፣ ከምንም በላይ ሰላማችንን አብዝተን በመጠበቅ እንዲሆን አደራ ለማለት እወዳለሁ።
በድጋሚ መልካም የመስቀል በዓል እንዲሆን እመኛለሁ።
አቶ ገ/መስቀል ጫላ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ
መስከረም 16/2018 ዓ.ም

More Stories
መሬት ውስን የተፈጥሮ ሀብት በመሆኑ በአግባቡ በመምራትና ከብክነት በመጠበቅ ቀጣይነት ያለዉን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
መስቀል የድህነት ምልክት መሆኑን የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ አህጉረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል ተናገሩ