መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንዳሻው ጣሰው መርቀው ከፈቱ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መዲና በሆሳዕና ከተማ የተመረቀው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንዳሻው ጣሰው፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የኘሮጀክቶች አስተባባሪ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ብርሀኑ ተስፋዬ፣ የክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው።
ማዕከሉ የዜጎችን እንግልት በማስቀረት ጊዜ፣ ወጪና ሀብት ከብክነት የሚታደግ ጥራት ያለው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል እንዲሁም የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን አንፃር የጎላ ፋይዳ እንዳለውም ተመላክቷል።
መሶብ በርካታ አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል በመሰብሰብ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ብቃት ያለው ተገልጋይን የሚመጥን አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ኢንሼቲቭ ነው።
በሆሳዕና ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጀመረው ይህ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ውስጥ 5 የፌደራል ተቋማት አገልግሎቶችን እንዲሁም 2 የክልል ተቋማት ከ20 በላይ የተለያዩ የአገልግሎት አይነቶችን ይሰጣል ተብሏል።
በማዕከሉ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት እንዲሁም የገቢዎች ቢሮ አገልግሎትን የሚሰጥ ሲሆን የኢሚግሬሽን፣ የንግድ ባንክ፣ ፖስታ አገልግሎት፣ ብሔራዊ መታወቂያ፣ ኢትዮ ቴሌኮም የመሳሰሉ የፌደራል ተቋማት አገልግሎትን በአንድ ስፍራ ማግኘት የሚያስችል ነው።
ቀጣይ ባሉ ጊዜያት አገልግሎቶቹን ወደ 60 የማሳደግ ዕቅድ መያዙም ታውቋል።
ዘጋቢ: አብደላ በድሩ
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንዳሻው ጣሰው መርቀው ከፈቱ

More Stories
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም
ጃፓን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ብራዚልን አሸነፈች
ከተሞች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዘው አገልግሎት መሥጠታቸው የተገልጋይና የአገልጋይ ግንኙነት ጤናማና እርካታ የተሞላበት እንዲሆን የሚያስችል መሆኑ ተገለጸ