ለሆሳዕና ማረሚያ ተቋም የህግ ታራሚዎች የተለያዩ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ
ሀዋሳ፡ መስከረም 14/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ሁሉ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ህብረት ሥራ ማህበር ለሆሳዕና ማረሚያ ተቋም የህግ ታራሚዎች የተለያዩ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
የተቋሙ ኃላፊዎችና ታራሚዎች በበኩላቸው ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።
የሁሉ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበር የቦርድ አባል አቶ ሀብታሙ ታረቀኝ በድጋፉ ወቅት የሀዲያ ዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓልን ከህግ ታራሚዎች ጋር መክበራቸው ደስታ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።
ማህበሩ ከገንዘብ ቁጠባና ብድር ሥራ ባሻገር በሰብዓዊ ተግባራት በመሳተፍ በርካታ የድጋፍ ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ሃብታሙ፥ በሆሳዕና ማረሚያ ተቋም ለሚገኙ 230 የህግ ታራሚዎች የተለያዩ ምግብና ምግብ-ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ ማበርከቱን ገልፀዋል።
የሆሣዕና ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ኮማንደር ዘውዱ ዱኖሮ በበኩላቸው የተለያዩ በጎ አድራጊዎችና ሃይማኖታዊ ተቋማት አንዲሁም ባለሀብቶች ሰፋፊ የድጋፍ ተግባራትን እያከናወኑ መሆናቸውን አንስተው፥ የሁሉ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ሥራ ማህበር ላደረገው መልካም ሥራ አመስግነዋል ።
የተቋሙ የህግ ታራሚዎች በሰጡት አስተያየት የሚደረጉ ድጋፎች ተገቢና የታራሚዎችን ችግር የሚያቃልል መሆኑን ገልፀው እገዛ ለደረጉ አካለትም ምስጋና አቅርበዋል።
ዘጋቢ: ኤልያስ ኤርሶ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
በግብርናው ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሠራ በኮንታ ዞን የኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ
ለ20ኛ ጊዜ “ዲሞክራሲያዊ አንድነት፤ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ቃል የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ለማክበር የጋሞ ዞን ም/ቤት የዝግጅት ሥልጠና እየሰጠ ነው
የእናቶችንና ህጻናት ሞት ለመቀነስና ጤና ለማሻሻል እናቶች የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን እገዛው የላቀ መሆኑ ተገለፀ