የሀዲያ ዘመን መለወጫ የያሆዴ በዓል የዕርቅ፣የአብሮነት፣የይቅርታ፣ የመሻገሪያ እና ሌሎች  በርካታ ባህላዊ ዕሴቶችን በውስጡ የያዘ ድንቅ ከኢትዮጵያ ባህሎች አንዱ ነው – የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

የሀዲያ ዘመን መለወጫ የያሆዴ በዓል የዕርቅ፣የአብሮነት፣የይቅርታ፣ የመሻገሪያ እና ሌሎች  በርካታ ባህላዊ ዕሴቶችን በውስጡ የያዘ ድንቅ ከኢትዮጵያ ባህሎች አንዱ ነው – የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሀዋሳ፣ መስከረም 13/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሀዲያ ብሄር ዘመን መለወጫ የያሆዴ በዓል በሀዲይ ነፈራ በድምቀት ተከብሯል።

በበዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) እንደገለጹት የሀዲያ ዘመን መለወጫ የያሆዴ በዓል የዕርቅ፣የአብሮነት፣የይቅርታ፣ የመሻገሪያ እና ሌሎች  በርካታ ባህላዊ ዕሴቶችን በውስጡ የያዘ ድንቅ ከኢትዮጵያ ባህሎች አንዱ ነው።

ኢትዮጵያ በህብረ ብሄራዊነት፣ ውብና ድንቅ ባህሎችና የተፈጥሮ ጸጋ የበለገች መሆኑን የገለጹት ዶክተር እንዳሻው ከእነዚህ አንዱ የሀዲያ ብሄር ዘመን መለወጫ የያሆዴ በዓል ነው ብለዋል።

የያሆዴ በዓል የዕርቅና የአብሮነት እንዲሁም ለልማት በአዲስ መልክ ቃላችንን የሚናድስበት ነው ብለዋል ዶክተር እንዳሻው።

ጽናትና ህብረት ለስኬት ማብቃቱን ተምረናል ያሉት ዶክተር እንዳሻው አሁንም ለሰላም፣ልማትና አንድነት መሰናክል የሚሆኑ ማነቆዎችን ለማጥፋት በአንድነት መቆም አለብን ብለዋል።

በገጠር ግብርና እና የኮሪደር ልማት አርሶአደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክሮ ይቀጥላሉ ያሉት ዶክተር እንዳሻው የሆሳዕና ከተማን ለነዋሪዎች እና እንግዶች ምቹ ለማድረግ እየተሰራ ያለው የኮሪደር ልማት ከግብ እንዲደርስ ህብረተሰቡ በተለይም ባለሀብቶች እያደረጉ ያለውን ተሳትፎ አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንዳሻው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

ዘጋቢ:-ሳሙኤል መንታሞ ከሆሳዕና ጣቢያችን