“አተካና” በሀዲያ ብሄር ዘንድ እጅግ ተወዳጅና ተናፋቂ ባህላዊ የምግብ ዓይነት እንደሆነ ተገለፀ

“አተካና” በሀዲያ ብሄር ዘንድ እጅግ ተወዳጅና ተናፋቂ ባህላዊ የምግብ ዓይነት እንደሆነ ተገለፀ

በያሆዴ በዓል ዋዜማ የሚዘጋጀው “የአተካና” ምሽት በሆሳዕና ከተማ በሀዲይ ነፈራ በድምቀት እየተከበረ ነው ።

አተካና በሀዲያ ብሄር ዘንድ እጅግ ተወዳጅና ብሄሩ ከሚታወቅበት ባህላዊ የምግብ ዓይነቶች አንዱ መሆኑ ተመላክቷል።

ይህ የምግብ ዓይነት ለታላላቅ በዓለት፥ ለከበረ እንግዳና ልዩ ድምቀት ለሚሰጣቸው ፕሮግራሞች የሚዘጋጅ የክብር ምግብ ነው።

“አተካናን” የሀዲያ እናቶች በረጅም ጊዜ በተካኑት ሙያ የእንሰት ውጤት በሆነው ቆጮና ቡላ እንዲሁም ከእንሰት ተዋጽኦ ቅቤ፣ ወተት፣ አይብ እና ሌሎችም የቅመማ ቅመም ዓይነቶች ተክለውበት ለመብላት በሚያስጎመጅ መልኩ የሚያዘጋጁት ባህላዊ የምግብ ዓይነት ነው።

በዚህ ደማቅ በሆነው የአተካና ምሽት የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እና በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የብሔሩ ተወላጆች ተገኝተዋል ።

ዘጋቢ: መንግሥቱ ፊጣሞ – ከሆሳዕና ጣቢያችን