6111 ok ለአርባ ምንጭ ስታድየም ግንባታ ባለ አራት ዲጅት የገቢ ማሰባሰቢያ ቁጥር ይፋ ተደረገ
ሀዋሳ: መስከረም 12/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ለአርባ ምንጭ ስታድየም ግንባታ ባለ አራት ዲጅት 6111 ok የገቢ ማሰባሰቢያ ቁጥር ይፋ መደረጉ ተገለፀ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ለአርባምንጭ አለም አቀፍ ስታዲዬም ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ 6111 ባለ አራት ዲጅት ቁጥር ይፋ ሆኗል።
በአርባ ምንጭ ከተማ ለሚገነባው ስታዲዬም አሻራችንን እናኑር ለሚሉ የልማቱ ደጋፊዎች ” 6111 Ok ” በይፋ ማስጀመሪያ መርሃግብር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር በአቶ ጥላሁን ከበደ አማኝነት ይፋ ተደርግል።
6111 ok በማለት የአርባምንጭ ስታድየም ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ ተሳትፎን ርእሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ መሪነት ስምፖዝየሙ ተሳታፊዎች ድጋፍ አደረግዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሸንካ በተገኙበት የተካሄደው ሲምፖዝየም፥ 6111 ok በማለት የሀብት ማሰባሰቢያ ተሳትፎ አድርገዋል።
በዚህም የስምፖዚየሙ ተሳታፊዎች በሙሉ የገቢ ማሰባሰቢያ ቁጥሩን በመጫን ድጋፍ አድርገዋል።
በመረሀግብሩ ላይ ርዕሰመስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የባህልና ስፖርት ምንስቴር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካን፣ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምሴ አድማሱ(ዶ/ር)፣ የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን መንዛን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፌዴራል፣ ክልል እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች እና ከጋሞ ዞን መዋቅሮች የተገኙ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ ፡ ገነት መኮንን- ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
በያሆዴ በዓል ወቅት የሚደረገው ሲምፖዚየም ለሀገር ልማትና አንድነት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ
በልዩ ልዩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ወደ ትምህርት ገበታ ሊመጡ ያልቻሉ ተማሪዎች መደገፍ እንደሚገባ ተጠቆመ
ጥራትና ወቅታዊነት ላይ ትኩረት ያደረገ የዕቅድ ዝግጅት አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ