ማሽቃሮ ”ለሰላምና ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው

ማሽቃሮ ”ለሰላምና ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው

ሀዋሳ: መስከረም 12/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማሽቃሮ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማሽቃሮ ”ለሰላምና ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የውይይቱ ዓላማ የቦንጋ ከተማ ዕድገት ባህላዊ እሴቶችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲሆንና የካፋ ባዮስፔር 15ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል ።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ፤ የቀድሞ የካፋ ንጉስ ዘውድ ወደ ካፋ በመጣበት ወቅት በዓሉን ለማክበር የታደሙ አካላት እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

የካፈቾ ዘመን መለወጫ በዓል በሚከበርበት ወቅት መልካም ተግባር ያከናወኑ አካላት የሚሞገሱበት መሆኑን አመላክተዋል ።

ቦንጋ ከተማ ከተቆረቆረ ረዥም ዘመናት ያስቆጠረ ቢሆንም በርካታ መሰረተ ልማት እጥረት ያለበት በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

ማሽቃሬ ባሮ የካፋ ተፈጥሮ ሀብትና ባህል ጋር የተቆራኘ እንደሆነም ተናግረዋል።

ማሽቃሬ ባሮ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

በፓናል ዉይይቱ በአፍሪካ የዩኔስኮ ተወካዮች፣ የናቡ አፍሪካ ኃላፊን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው።

ዘጋቢ : ሀብታሙ ኃይሌ – ከቦንጋ ጣቢያችን