“ለጎፋ ዞን አንድነትና ብልፅግና በጋራ እሮጣለሁ”በሚል መሪ ቃል የጎፋ ጋዜ ማስቃላ እና የኦይዳ ዮኦ ማስቃላ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ
ሀዋሳ፡ መስከረም 12/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) “ለጎፋ ዞን አንድነትና ብልፅግና በጋራ እሮጣለሁ” በሚል መሪ ቃል የጎፋ ጋዜ ማስቃላ እና የኦይዳ ዮኦ ማስቃላ ምክንያት በማድረግ በጎፋ ዞን ታላቁ ሩጫ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።
የሩጫ ውድድሩ ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ ከፍ ብላ እንድትታይ ከሚያደርጓት ዘርፎች አንዱ ሲሆን የኢትዮጵያዊያን የጥንካሬና የአሸናፊነት መገለጫ የሆነው የሩጫ ውድድር “ለጎፋ ህዝብ አንድነትና እድገት እሮጣለሁ” በሚል መሪ ሃሳብ በሣውላ ከተማ ተካሂዷል።
በውድድሩ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስቴር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቦጋለ ፈይሳ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ውድድሩ የጎፋ ዞን አስተዳደር ከፋን ኢትዮጵያ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን 8 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው።
ዘጋቢ: አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም
ጃፓን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ብራዚልን አሸነፈች
ከተሞች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዘው አገልግሎት መሥጠታቸው የተገልጋይና የአገልጋይ ግንኙነት ጤናማና እርካታ የተሞላበት እንዲሆን የሚያስችል መሆኑ ተገለጸ