በኢፌደሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስተር ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ የተመራ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ወደ ጎፋ ዞን ገቡ

በኢፌደሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስተር ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ የተመራ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ወደ ጎፋ ዞን ገቡ

በኢፌደሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዶክተር ተስፋዬ በልጅጌ ጨምሮ፥ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባቴ፣ የፋን ኢትዮጵያ መስራችና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፋንቱ ሜጊሶ እና የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ልዑካኑ ወደ ዞኑ ሲደርሱ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ ፣ የዞኑ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጋሻለው እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ልዑካን ቡድኑ በዞኑ በሚኖራቸው ቆይታ “ለጎፋ ዞን አንድነትና ዕድገት እሮጣለሁ” በሚል መሪ ቃል በሚደረገው ታላቁ ሩጫ እንደሚሳተፉና የጎፋ ጋዜ ማስቃላ እና የኦይዳ ዮኦ ማስቃላ በዓልን ለማክበር መሆኑ ተገልጿል።

ዘጋቢ: አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን