በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ መስከረም 11/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተሮት ዳይሬክተር ዶ/ር ይድነቃቸው ደዳቸው ተናገሩ::
በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተሮት ዳይሬክተር ዶክተር ይድነቃቸው ደዳቸው ተናገሩ::
በሆስፒታሉ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር መመርመሪያ ማሽን አገልግሎት በ I-CUP ኢትዮጵያ ድጋፍ ማስጀመሩም ተገልጿል።
የንግስት ኤሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በውስን የህክምና ዘርፎች የጀመረውን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ከጊዜ ወደጊዜ እያስፋፋና እያሻሻለ የወቅቱ የህክምና ቴክኖሎጂ ባፈራቸው ዘመናዊ መሳሪያዎች እየታገዘ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ሆስፒታሉ የህክምና አቅሙን በማጎልበት ከዚህ ቀደም ያልተጀመሩ የህክምና አገልግሎቶችን ብቃት ባለው የሰው ኃይልና በዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች በተደራጀ መልኩ ጥራት ያለውን የጤና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም ዶክተር ይድነቃቸው ገልጸዋል።
የእናቶች ወሊድ አገልግሎትን ጨምሮ የድንገተኛ፣ ተመላላሽና ተኝቶ ህክምና አገልግሎት በሆስፒታሉ ስፔሻሊስት ሀኪሞች በተሟላ የላቦራቶሪ ምርመራ እየተሰጠ መሆኑንም አመላክተዋል።
በተለይም ሆስፒታሉ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ህክምና አገልግሎት በስፔሻሊስት ሀኪሞች መስጠት መጀመሩ ትልቅ ስኬት መሆኑንም ተናግረዋል::
አሁን ላይ ለተገልጋዮች የፎረንሲክ ምርመራ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ያስታወቁት ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተሩ የአገልግሎት ጥራትና ውጤታማነትን በማሳደግ በቀጣይ የሆስፒታሉን አቅም ይበልጥ በማጎልበት የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።
በሆስፒታሉ የማህጸን እና ጽንስ ክፍል ኃላፊ ዶክተር አብይ አበራ እንደገለጹት የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር በአግባቡ ክትባቶችን ከልተወሰዱ ገዳይ በሽታ በመሆኑ አስቀድሞ ለመከላከል በሆስፒታሉ አገልግሎት መስጠት የጀመረው መመርመሪያ ማሽን እገዛ የላቀ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዶ/ር አብይ አክለውም ማሽኑ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ የታካሚዎችን እንግልት እና የገንዘብ ወጪ የሚያስቀር እንደሆነም አመላክተዋል።
በ I-CUP ኢትዮጵያ ፕሮግራም አስተባባሪና የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስት ሀኪም ዶክተር ህዝቅኤል ጴጥሮስ በበኩላቸው መመርመሪያ ማሽን ድጋፍ ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር በአግባቡ ክትባቶችን በመውሰድና የቅድመ ምርመራ ማድረግ በወቅቱ መታከም ከተቻለ በቀላል ህክምና የሚድን በሽታ እንደሆነ ጠቁመው ፣ከቅድመ ማህጸን ጫፍ ካንሰር ምርመራ አልፎ ስር ከሰደደ ግን ለሞት የሚደረግ ነው ብለዋል።
በሆስፒታሉ ድጋፍ የተደረገው የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር መመርመሪያ ማሽን የሚከሰቱ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል አስተዋጽኦ የላቀ እንደሆነም ዶክተር ህዝቅኤል ጠቅሰዋል።
ዘጋቢ: በየነ ሰላሙ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም
ጃፓን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ብራዚልን አሸነፈች
ከተሞች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዘው አገልግሎት መሥጠታቸው የተገልጋይና የአገልጋይ ግንኙነት ጤናማና እርካታ የተሞላበት እንዲሆን የሚያስችል መሆኑ ተገለጸ