የህዝቡን ሰላምና አንድነት በማጠናከር የብሄረሰቡን ቋንቋና ውብ ቱባ ባህላዊ እሴቶችን ለትውልድ ለማሸጋገር በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ

የህዝቡን ሰላምና አንድነት በማጠናከር የብሄረሰቡን ቋንቋና ውብ ቱባ ባህላዊ እሴቶችን ለትውልድ ለማሸጋገር በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ መስከረም 11/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) የህዝቡን ሰላምና አንድነት በማጠናከር አብሮ በመሥራት የብሄረሰቡን ቋንቋና ውብ ቱባ ባህላዊ እሴቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል ለትውልድ ለማሸጋገር በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የጠምባሮ ባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም ተሳታፊ የሆኑ የብሔረሰቡ ተወላጆች ተናገሩ።

ኢትዮጵያ ታላቁን የህዳሴ ግድብ ገንብታ በማጠናቀቅ እንደ ሀገር ድልን በመቀዳጀት ለዓለም መሥራት እንደምትችል ባሳየችበት ማግስት የጠምባሮ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ የማሳላ(ማሪሾ) በዓል መከበሩ ልዩ ደስታ እንደፈጠረባቸው ጠቁመዋል።

በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ለመጀመሪያ ጊዜ “የህዝቦች አንድነት ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለው የጠምባሮ ብሔረሰብ ባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም፥ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተሳተፉ የብሄረሰቡ ተወላጆች ብሔረሰቡ ከጥንት ጀምሮ የህዝብን ሰላምና አንድነት የሚያጠናክሩ፣ ለልማት የሚያነሳሳ (የጉዳ ጎንዶሮ ) የባህላዊ የዕርቀ ሥርዓትን ጨምሮ በርካታ አስተማሪ የሆኑ ባህላዊ እሴቶች ያሉበት ነው ብለዋል ።

በሲምፖዚየሙ የተለያዩ ምሁራን ባህልንና ቋንቋን ከማሳደግ አኳያ ያቀረቡት የጥናታዊ ጽሑፍ የህዝብን አንድነት ለማጠናከር የሚያስችሉና እጅግ አስተማሪ መሆናቸውን አስተያየት ሰጭዎቹ ጠቁመው፥ ይህ የመጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን በቀጣይ በምሁራን በኩል የብሄረሰቡን ባህላዊ እሴቶች ሳይበረዝ ለትውልድ ለማሸጋገር የሚያስችሉ የጠምባሮን ሰላም፣ አንድነት፣ እድገትና ልማትን ለማፋጠን አጋዥ የሆኑ ጥናታዊ ሥራዎችን የማከናወን ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገበል ሲሉ አሳስበዋል።

ባህላዊ እሴቶችን በየደረጃው ያሉ የመንግሥት ባለድርሻ አካለት አጉልተው የሚያሰዩ፣ ተፈጥሯዊና ሰው ሰረሽ መስህቦቻችንና ቋንቋን በሚፈለገው ደረጀ ለማልማት፣ ለማሳደግና ለማስተዋወቅ በትኩረት መሥራት ይጠበቃልም ነው ያሉት።

ሥራው ለመንግሥት አካለት ብቻ የሚተው ባለመሆኑ ሁሉም የብሄረሰቡ ተወላጆች ሰላምና አንድነት በማጠናከር ተባብሮ በመሥራት ውብ የሆኑ ባህላዊ እሴቶችን ማሳደግ እንዲቻል ሁሉም የድርሻውን ሊንወጣ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ።

የጠምባሮ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ መሰላ የመጀመሪያው የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም ብሔረሰቡ በብልጽግና መንግሥት ራሱን በራሱ የማስተዳደር ዕድል ካገኘበትና ኢትዮጵያ እንደሀገር ታላቁን የህዳሴ ግድብ በማጠናቀቅ ድል በመቀዳጀት መሥራት እንደምትችል ለዓለም ባሳየችበት ማግስት መከበሩ ልዩ ደስታ እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል ።

ዘጋቢ: ሙሉነሽ ለማ – ከሆሳዕና ጣቢያችን