የህዝበ ውሳኔውን አጠቃላይ ውጤት በትዕግስት እንጠብቃለን – መራጮች
ሀዋሳ: ሰኔ 13/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) በወላይታ ዞን የተካሄደው ድጋሚ ህዝበ ውሳኔ አጠቃላይ የድምፅ ውጤት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስኪገለፅ ድረስ በትዕግስት መጠበቅ እንደሚገባ በሶዶ ከተማ በህዝበ ውሳኔው የተሳተፉ መራጮች ተናገሩ::
በሶዶ ከተማ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ጊዚያዊ ውጤት ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ መራጮች ጊዚያዊ ውጤቱን እየተመለከቱ ይገኛሉ::
ጊዚያዊ ውጤቱን ሲመለከቱ ደሬቴድ ያነጋገራቸው መራጮች ምርጫው በሠላም በመጠናቀቁ ደስተኞች ነን ብለዋል::
በምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደት ተጠናቆ ጊዚያዊ ውጤቶችም መለጠፋቸው አስፈፃሚዎች ሥራቸውን በተያዘላቸው የጊዜ ሰለዳ መሠረት እያከናውኑ እንደሚገኙ የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል::
በጊዚያ ውጤቱ ደስተኞች ነን ያሉት መራጮቹ በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አጠቃላይ የምርጫውን ውጤት ይፋ እስከሚያደርግ ድረስ በትዕግስት መጠበቅና ውጤቱንም በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል::
ዘጋቢ: ማሬ ቃጦ
More Stories
የማታ 1፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም
ጃፓን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ብራዚልን አሸነፈች
ከተሞች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዘው አገልግሎት መሥጠታቸው የተገልጋይና የአገልጋይ ግንኙነት ጤናማና እርካታ የተሞላበት እንዲሆን የሚያስችል መሆኑ ተገለጸ