በወላይታ ዞን ድጋሚ የሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ  ሠላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ተደርጓል – አቶ ተስፋዬ ጎአ

በወላይታ ዞን ድጋሚ የሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ  ሠላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ተደርጓል – አቶ ተስፋዬ ጎአ

ሀዋሳ፡ ሰኔ 10/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም በወላይታ ዞን ድጋሚ የሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ  ሠላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት መደረጉን የወላይታ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጎአ ገለፁ::

አቶ ተስፋዬ በተለይም ለደሬቴድ እንደተናገሩት በወላይታ ዞን ዳግም በሚካሄደው የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ላይ ህዝቡ ዴሞክራሲያዊ የመምረጥ መብቱን ተጠቅሞ በነቂስ መሳተፍ እንዲችል የፀጥታው መዋቅር የሚጠበቅበትን ለመወጣት ዝግጅቱን አጠናቋል ነው ያሉት::

በዕለቱ ህዝቡ ዴሞክራሲያዊ መብቱን እንዳይጠቀም በተለያየ መንገድ የማደናቀፍ ሥራ ማድረግ የሚፈልጉ አካላት ካሉ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ለምርጫው ሠላማዊነት፣ ፍትሀዊነት እና ዴሞክራሲያዊነት የድርሻውን እንዲያበረክት ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል::

ዘጋቢ: ማሬ ቃጦ