የልማት ክፍታቶችን ለመሙላትና የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 04/2015 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጎፋ ዞን እድገትና ልማት ማህበር በዞኑ ያሉ የልማት ክፍታቶችን ለመሙላትና የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የልማት ማህበሩ የአዲስአበባ ቅርጨፍ ጽ/ቤት የ2015 በጀት ዓመት የ10 ወራት አፈጻጸም የማህበሩ አባለት በተገኙበት ገምግሟል።
ከዚህ በተጓዳኝ በዞኑ ኡባ ደብረፀሐይ ወረዳ ዛባ ቀበሌ በጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸውና ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ገቢ የማሰባሰብ ሥራዎችም ተሰርተዋል።
የጎፋ እድገትና ልማት ማህበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደግፌ ኃ/ማርያም እንደገለፁት፥ ልማት ማህበሩ ከተለያዩ አጋሮች፣ ረጂ ድርጅቶት እንዲሁም አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አከባቢዎች ከሚገኙ የልማት ማህበሩ አባለት 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የሚገመት ቁሳቁስ አሰባስቦ ለጎርፍ ጉዳት ሰለባ ለሆኑ የዛባ ቀበሌ ነዋሪዎች ድጋፍ አድርጓል።
ከተለያዩ አካላት በተሰበሰበው 1 ሚሊየን ብር በጎርፍ አደጋ ጉደት የደረሰበቸውን ትምህርት ቤቶች ለመገንባት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
ልማት ማህበሩ በትምህርት፣ በጤና እንዲሁም ሌሎችንም የሰብአዊ ድጋፍ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ሥራ አስኪያጁ አስታውቀዋል።
በ2015 ዓ.ም በጎፋ ዞን ዛላና ኡባደብረፀሐይ ወረደ ተከስቶ በነበረው ድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ200ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉንም አቶ ደግፌ ተናግረዋል።
በዘንድሮ ዓመት በዞኑ በ8ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 43 ተማሪዎችን ሎጼ በሚባል ትምህርት ቤት በሶስት ሴሚስቴር በዘጠነኛ ክፍል እያስተማረ ይገኛል።
ልማት ማህበሩ ከተቋቋመ ዘንድሮ 4ኛ ዓመቱን የያዘ ስሆን አዲስአበባን ጨምሮ በተለያዩ አከባቢዎች ቅርጨፍ ጽ/ቤቶችን ከፍቶ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል ።
በጎፋ ዞን ኡባደብረፀሐይ ወረደ ዛባ ቀበሌ ሚያዝያ 26 ቀን 2015 ምሽት ላይ ተከስቶ በነበረው የጎርፍ አደጋ የ21 ሰዎች ህይወት ማለፉ የሚታወስ ሲሆን በንብረትና በሰብል ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።
ዘጋቢ፡ ጌታሁን አንጭሶ
More Stories
በከተሞች የሚስተዋሉትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ለሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ሰፊ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ
ማህበራዊ ሚዲያን በአግባቡ በመምራት እና በመጠቀም የአካባቢን ገጽታ መገንባት እንደሚገባ ተጠቆመ
የአዳሪ ትምህርት ቤቶች መስፋፋት ጥራት ያለው ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት እንደሚያስችል ተገለጸ