የፍትህ ተቋማትና ፍርድ ቤቶች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመሰጠት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የጎፋ ዞን የፍትህ ዘርፍ ተቋማት እና የፍርድ ቤቶች የማጥራት ሂደት ማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ ውይይት በተካሄደበት ወቅት የጎፋ ዞን የሕዝብ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ ወ/ሮ ሀብታምነሽ ግራአዝማች የፍትህ ተቋማትና ፍርድ ቤቶች ዉጤታማ፣ ቀልጣፋና አሜነታ ያለውን አገልግሎት ለህብረተሰቡ በመሰጠት የሚነሱ ቅሬታዎችን መፍታት እንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡
የጎፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ፀጋዬ ጽጌ በየደረጃው የሚገኙ ፍርድ ቤቶችና የፍትህ አካላት የማጥራት ሂደት ለህብረተሰቡ የጠራ የፍትህ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል አግባብ የሰለጠነ የሰው ሀይል በማደራጀትና በቴክኖሎጂ የታገዙ ስራዎችን ለመሰራት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል ፡፡
የፍትህ ተቋማት ለህብረተሰቡ በታማኝነት ማገልገል እንዳለባቸው አንስተው ከስነ-ምግባር አኳያ የሚነሱ ቅሬታዎችን በቀጣይ ለመፍታት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ብላቴ ተናግረዋል ፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በፍትህ ተቋማት የሚስተዋሉ የፍትህ አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ጠቁመው የሰው ኃይል እጥረትና የአቅም ውስንነት ለማሻሻል ታቅዶ መስራት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
በመድረኩ የተገኙት የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ምናሴ ኤልያስ ለተነሱ ጥያቂዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
በመንግስትና በፓርቲ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዘገቡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታወቀ
“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ህብረት ፓርቲ አመራርና አበላት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከናወኑ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን በኮላንጎ ከተማ እያካሄደ ነው