ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን ለማሳደግ በትኩረት መሰራት እንደሚገባ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ዓመታዊ የዕቅድ አፈፃፀምና ግምገማ መድረክ በሶዶ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የጤና ፕሮግራም ዘርፍ ኃላፊ አቶ መና መኩሪያ በቀጣይ የልማት ፕሮግራሞች በይበልጥ ጥራቱ የተጠበቀ ከማድረግ ረገድ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ በበኩላቸው ባለፈው በጀት ዓመት በበሽታ መከላከል የእናቶችንና የሕፃናትን ሞት በመቀነስ ረገድ ጠንካራ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
ዘጋቢ: ፀሐይ ጎበና – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
በመንግስትና በፓርቲ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዘገቡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታወቀ
“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ህብረት ፓርቲ አመራርና አበላት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከናወኑ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን በኮላንጎ ከተማ እያካሄደ ነው