‎ወጣቶች የክረምት ጊዜያቸውን ህዝብን ሊጠቅሙ በሚችሉ በጎ ተግባራት ላይ በመሳተፍ ማሳለፍ እንደሚገባ ተገለጸ

‎ወጣቶች የክረምት ጊዜያቸውን ህዝብን ሊጠቅሙ በሚችሉ በጎ ተግባራት ላይ በመሳተፍ ማሳለፍ እንደሚገባ ተገለጸ

‎‎”በጎነትና መልካምነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም ከተማ አቀፍ የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ ተካሂዷል።

‎የይርጋጨፌ ከተማ ምክትል ከንቲባና ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ታምራት ሚጁ እንደተናገሩት የክረምት የወጣቶች አገልግሎት ትውልድ ላይ የሚሠራ ሥራ ነው ብለዋል።

‎‎ከተማ አስተዳደሩ በሁሉም ዘርፍ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደረግም ነው የተናገሩት።

‎ደም ሲለግሱ ያገኘናቸው በጎ ፈቃደኞችም ደም ለግሰን የበርካታ እናቶችን ሞት ማስቀረት ስለምንችል ደስተኞች ነን ብለው በክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት  በተለያዩ ዘርፎች እንደሚሰማሩ ተናግረዋል፡፡

‎‎የይርጋጨፌ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባሃሩ ማሞ በበኩላቸው የ2017 ዓ/ም የክረምት በጎ አገልግሎት በተመረጡ አሥራ አምስት ዘርፎች እንደሚከናወን የገለፁ ሲሆን ከ6 ሺህ በላይ ወጣቶችን በማሳተፍ ከ7 መቶ ሺህ በላይ የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ለማድረግና ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ከመንግስት ይወጣ የነበረውን ለማዳን ይሠራል ነዉ ያሉት።

‎‎በመርሃ ግብሩ የችግኝ ተከላ የቤት ግንባታና የክረምት ትምህርት ማስጀመሪያ ተግባራትም ተከናውነዋል።

‎ዘጋቢ፡- አብነት አበበ: ከይርጋጨፌ ጣቢያችን