የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ በኣሪ ዞን በደቡብ ኣሪ ወረዳ በኮመር ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ከ6 መቶ ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸውን የዕለት ደራሽ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ
በአሪ ዞን በደቡብ ኣሪ ወረዳ በኮመር ቀበሌ ሐምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ከፍተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከስቶ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ ከአካባቢው የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያለሆኑ ተቋማት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ ይገኛሉ።
ድጋፉን ያስረከቡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ በመሬት መንሸራተት ምክንያት በተፈጠረ አደጋ እጅግ ማዘናቸውን ገለጸው በቦታው ተገኝተን ለተፋናቀሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ከ6 መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ ምግብና ምግብ ነክ ያለሆኑ ቁሳቁሶች፣ የንጽህና መጠበቂያዎችና ልብሶችን ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል ።
ቢሮውም በአደጋው ተፈናቅለው የሚገኙ ሴቶችና ህጻናትን ከግንዛቤ ውስጥ ባስገባ መልኩ ድጋፉን ማቅረቡን አንስተው በቀጣይም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ተከታታይ ድጋፍ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የቢሮ ኃላፊዋ ወሮ ካሰች ኤልያስ አብራርተዋል ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፈ ኃላፊ ወ/ሮ እቴነሽ በየነ በደረሰው ተፈጥሯዊ አደጋ ማዘናቸውን ገለጻው ለሰብዓዊነት ቅድሚያ በመስጠት ወንድማማችነትንና እህትማማችን የሚንገለለጽበት በመሆኑ የኖረ ባህላችንን በማጠናከር የተጎዱ ወገኖቻችን መጠየቅ ያሰፈልጋል ስሉ ጥሪ አቅርበዋል ።
የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ አስፈላጊ ሰብዓዊ ድጋፎች በማቅረብና በማስተባበር እሰከ ቦታው ድርስ በመምጣት ከጎናችን ለሆኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ እንዲሁም ሌሎችንም አመስግነው ተፈናቃዮችን ለማቋቋም በሚደረገው ጥራት ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል ።
ዘጋቢ : ጄታ ታገሠ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ወጣቶች የክረምት ጊዜያቸውን ህዝብን ሊጠቅሙ በሚችሉ በጎ ተግባራት ላይ በመሳተፍ ማሳለፍ እንደሚገባ ተገለጸ
የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን በማስፋፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ገለጸ
የቅዱስ ገብርኤል በአለ ንግስ ያለምንም የፀጥታ ችግር በታላቅ ድምቀት ተከብሮ መዋሉን የጋሞ ዞን ፖሊስ ገለፀ