የቅዱስ ገብርኤል በአለ ንግስ ያለምንም የፀጥታ ችግር በታላቅ ድምቀት ተከብሮ መዋሉን የጋሞ ዞን ፖሊስ ገለፀ

የቅዱስ ገብርኤል በአለ ንግስ ያለምንም የፀጥታ ችግር በታላቅ ድምቀት ተከብሮ መዋሉን የጋሞ ዞን ፖሊስ ገለፀ
‎
‎ህብረተሰቡም ላደረገው ቀና ትብብር የዞኑ ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል።
‎
‎የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብረሀም ቡኤ፤ የመልዓኩ የቅዱስ ገብርኤል በአል በዞኑ ባሉ አድባራት ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ መዋሉን አስታውቀዋል።
‎
‎አክለውም ህብረተሰቡ የትራፊክ አደጋም ሆነ የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር ላደረገው ቀና ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።
‎
‎በተመሳሳይ ታሪካዊው እና በፌደራል ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን የተመዘገበው የኤሊው ቅዱስ ገብርኤል በአለ ንግስ በሰላም ተከብሮ መዋሉን የዳራማሎ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ቡካ ቡላቻ አስታውቀዋል።
‎
‎ገዳሙ ታሪካዊ በመሆኑ በአሉን ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን የተሳተፉ ሲሆን እንግዶችን በመቀበልና በመሸኘት ህብረተሰቡ ላደረገው ቀና ትብብር አመስግነዋል።
‎
‎ዘጋቢ፡ ገነት መኮንን – ከአርባምንጭ ጣቢያችን