ወጣቶች የክረምት ወራት የእረፍት ጊዜያቸውን በልዩ ልዩ የስፖርት ውድድሮች ከመሳተፍ ባሻገር በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ላይ በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው የቀቤና ልዩ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ገለፀ
የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ የቴኳንዶ ውድድር በልዩ ወረዳው በሚገኙ በ5 ማዕከላት መካከል በወልቂጤ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጁሃር ጀማል በዚህ ወቅት እንደገለፁት በልዩ ወረዳው ወጣቶች በልዩ ልዩ ስፖርታዊ ውድድሮች እንዲሳተፉ በማስቻል ጤናማና ንቁ ዜጋ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡
ወጣቶች ከሱስ በመራቅ በአካባቢያዊና ሀገራዊ የልማትና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ስፖርት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ያሉት አቶ ጁሃር፤ በዚህ ረገድ በልዩ ወረዳው የሚገኙ የወርልድ ቴኳንዶ ማዕከላት በችግኝ ተከላ፣ በደም ልገሳ፣ በአካባቢ ፅዳትና በሌሎችም የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም የክረምት ወራት የእረፍት ጊዜያቸውን በልዩ ልዩ የስፖርት ውድድሮች ከመሳተፍ ባሻገር በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸውም ሃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በልዩ ወረዳው በተያዘው የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት በ14 ዘርፎች ከ49 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ከመንግስት ይወጣ የነበረውን 25 ሚሊየን ብር የሚገመት ሃብት ለማዳን ግብ ተጥሎ ወደ ተግባር መገባቱንም ሃላፊው አስረድተዋል፡፡
በልዩ ወረዳው ወጣቶች ዘንድ የወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ከጊዜ ወደ ጊዜ ባህል እየሆነ መምጣቱንም ተናግረዋል፡፡
አቶ አባስ ጅላሉ የቀቤና ልዩ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ሃላፊ ሲሆኑ በልዩ ወረዳው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በስፖርት ልማት ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል፡፡
የቴኳንዶ ስፖርት ወጣቶች የተሻለ ስብዕናና ስነ ምግባር እንዲኖራቸው የሚያስችል በመሆኑ በልዩ ወረዳው ለሚገኙ ማዕከላት ልዩ ትከረት ተሰጥቶ የቅርብ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል አቶ አባስ፡፡
በተለይም በወርልድ ቴኳንዶ ዘርፍ ከልዩ ወረዳውና ከክልሉ በተጨማሪ በሀገር አቀፍ ደረጃ ውጤታማ የሆኑ ስፖርተኞችን ማፍራት መቻሉን አቶ አባስ አስረድተዋል፡፡
በልዩ ወረዳው በሚገኙ በ5 ማዕከላት መካከል እየተካሄደ የሚገኘው የውስጥ ለውስጥ የቴኳንዶ ውድድሩ ለ2 ቀናት የሚቆይ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ዘጋቢ፡ ጅላሉ ፈድሉ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
ወጣቶች የክረምት ጊዜያቸውን ህዝብን ሊጠቅሙ በሚችሉ በጎ ተግባራት ላይ በመሳተፍ ማሳለፍ እንደሚገባ ተገለጸ
የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን በማስፋፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ በኣሪ ዞን በደቡብ ኣሪ ወረዳ በኮመር ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ከ6 መቶ ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸውን የዕለት ደራሽ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ